የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ


የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ5 የስራ መደቦች የውጪ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ከየካቲት 23-25 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ፈተና መስጠቱ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሰረት በወቅቱ ፈተናውን ከወሰዱት ዕጩ ተወዳዳሪዎች መካከል በባለስልጣኑ ድረ-ገፅ የስም ዝርዝራቸው የተመለከቱት፤
1. በመሀንዲስI(ለውሃናለፍሳሽ) የስራ መደብ ላይ የስም ዝርዝራቸው የተመለከቱት ሚያዝያ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ሰዓት የማጣሪያና የቃል ፈተና የሚሰጥ መሆኑን፤
2. በስታንዳርድ አፈፃፀምና ምዘና ኦፊሰር፣ ጀማሪ ኬሚስትና ጀማሪ ባዮሎጂስት ደግሞ ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ሰዓት የማጣሪያና የቃል ፈተና የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

No Title Link
1 Water, sewerage and standard Download
2 Chemist and biology Download