የኘሮጀክቱ ሥም፡    ለውኃ መስመር ዝርጋታ የሚያገለግሉ ቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- በከተማው ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየተስፋፉ የሚገኙ ከመሆኑም በላይ አካባቢዎቹ የተቆራረጠ የውኃ አግልግሎት እያገኙ ይገኛሉ በመሆኑም ይህ የቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ እነዚህን አካባቢዎች የንጹ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ማድረግ ዋነኛ ዓለማው ይሆናል፡፡

የኘሮጀክትግብ፡- ለውኃ መስመር ዝርጋታ የሚያገለግሉ ቧንቧና መገጣጠሚያዎች ግዥ በመፈጸም የተለያዩ አካባቢዎችን የንጹ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል መስመር ዝርጋታ ሥራ ማዋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 • ለውኃ መስመር ዝርጋታ የሚያገለግል ቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ መፈጸም

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

 • በ2006 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

 • በ2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 300,000,000 ይፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

የአዲስ አበባ ከተማ በአሁን ሰዓት በአብዛኛው ደረጃቸውን የጠበቁ ሪል እስቴቶች ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም የግል ቬላ ቤቶች እየተገነቡባት ያለች መዲና ሆናለች፡፡ በዚህም በአንዳንድ አካባቢዎች አዲስና በከፍተኛ ደረጃ በመስፋፋት ላይ የሚገኙ ከመሆናቸው አንጻር ከፍተኛ የሆነ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ይታይል፡፡  ይህንን ችግር በኮንትራክተሮች ብቻ በማሰራት የማንወጣው ሲሆን ለዚህም በየቅ/ጽ/ቤቱ የራስ ኃይል ቡድን ተቋቁሞ ይህን ሥራ በስፋት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ለዚህ ቡድን እንደ ግብዓት ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ የቧንቧና መገጣጠሚያ አቅርቦት ነው፡፡

ከዚህ አንጻር የኘሮጀክቱ ዋና ተግባር ግዥ ለመፈጸም የሚያስችሉ ሰነዶችን በማዘጋጀት የውኃ ቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ መፈጸም ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

በከተማው ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየተስፋፉ የሚገኙ ከመሆኑም በላይ አካባቢዎቹ የተቆራረጠ የውኃ አግልግሎት እያገኙ ይገኛሉ በመሆኑም ይህ የቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ እነዚህን አካባቢዎች የንጹ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ማድረግ ዋነኛ ዓለማው ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

ኘሮጀክቱ በዋና ዓላማው ላይ መሠረት ያደረገ ግብ ይኖረዋል፡፡ ይኸውም የውኃ መስመር ዝርጋታን በማስፋፋት በከተማው የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የንጽሁ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የውኃ መስመር ዝርጋታው በሚከናወንበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን በአነስተኛ ወጪ መ/ቤቱ የንጹህ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ማድረግ ያስችላል፡፡ በዚህም፡

 • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
 • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
 • የአካባቢ ብክለትን ማስወገድና የተሟላ ጤና እንዲኖር ያደርጋል፡፡
 • የፀዳች አዲስ አበባ ብሎም ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ እድገት የተመቸች ከተማ እንድትኖረን ያደርጋል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

 • የውኃ ቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ ማጠናቀቅ፣

ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች

ፕሮጀክቱን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃሉ፡፡

ሀ/ ሥጋቶች

 • አቅራቢዎች ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ያለማቅረብ፣
 • በቂ አቅራቢዎች አለመኖር፣

ለ/ ምቹ ሁኔታዎች

 • ሥራውን ተግባራዊ ለማድርግ የመንግስት ቁርጠኝነት
 • በአካባቢው የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት፤
 • ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች
ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
38 የውኃና ፍሳሽ ቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ ፕሮጀክት   100,000,000 100,000,000 0 0 0
38.1 ለውኃና ፍሳሽ ቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ ክፍያ መፈጸም 300,000,000 100,000,000 100,000,000 ከዕቃ አቅርቦቱ ጋር በተያያዘ በ2008 በጀት ዓመት ለሚከፈል ክፍያ የተጠቀሰው ብር ተይዟል፡፡