ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ለ25,553 አባወራዎች የፍሳሽ መስመር ቅጥያ በማከናወን ዘመናዊ የፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለ22,874 አባወራዎች የፍሳሽ መስመር ለመቀጠል ታቅዶ ለ25,553 አባወራዎች ቅጥያ በማከናወን የፍሳሽ መስመር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
በተያያዘም በበጀት ዓመቱ በቁጥር 125 የፍሳሽ መስመር ጥገና ለማከናወን በዕቅድ ተይዞ በቁጥር 1,619 (የዕቅዱን 1,295%) ለማከናወን ተችሏል፡፡
ለዕቅድ አፈፃፀሙ መጨመር ዋነኛ ምክንያትም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወኑ የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራዎች መጨመር ለፍሳሽ መስመር ስብራት መጨመር በምክንያትነት ተገልጿል፡፡
Recent Comments