ባለስልጣኑ እውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር ያዘጋጀው ለፍሳሽ ተሽከርካሪ ኦፕሬተሮች እና ረዳቶች እንዲሁም ለሌሎች ባለሙያዎች ነው፡፡

በዕውቅና እና ምስጋና መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ እንደገለጹት፤ ዘርፉ የከተማችን ውበት እና ጽዳት የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ እና አሁን ባለው የከተማችን ነባራዊ ሁኔታ አብዛኛው ፍሳሽ ቆሻሻ በተሸከርካሪ የሚነሳ በመሆኑ ያለዘርፉ ሰራተኞች ይህንን ከግብ ማድረስ ፈጽሞ የማይታብ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኢ/ር ዘሪሁን የዘርፉ ሰራተኞች ህዝብ ለማገልገል ለከፈሉት መስዋትነት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በባለስልጣኑ የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና/ ስራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ አርጋው በበኩላቸው የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራር ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የእውቅና መርሀ ግብረ መዘጋጀቱን ገልጸው፤ ፕሮግራሙ እንዲሳካ እገዛ ላደረጉት ለሁሉም አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዕወቅና የተቸራቸው ሰራተኞች የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብሩ ከፍያለ መነሳሳት እንደፈጠራበቸውና በቀጣይም ስራቸውን በትጋት እና በሃላፊነት ስሜት በመስራት ህብረተሰቡን ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ባለስልጣኑ ፍሳሹን የመሰብሰብ ስራ በላቀ ደረጃ ለመፈጸም በ15 ሚሊዮን ዶላር 90 የፍሳሽ ተሸከርካሪዎችን በቅርቡ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡