የኘሮጀክቱ ሥም፡    በተለያዩ የኮንዶሚኒየም ግንባታ በሚከናወንባቸው ቦታዎች የመለስተኛ ጉድጓዶች ቁፋሮ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-በአዲስ አበባ ኮንደሚኒየም አካቢዎች

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- ጉድጓዶቹን በመቆፈርና ወደ ሲስተም በማስገባት ተጨማሪ ውኃ ለከተማዋ ህብረተሰብ ማቅረብ ነው፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-በተለዩ የውኃ መገኛ አካባቢዎች የ25 መለስተኛ ጉድጓዶች ቁፋሮና ተያያዥ ሥራዎች ይጠናቀቃል፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 • የጂኦፊዚካልና ሀይድሮሎጂካል ጥናት፣
 • የስርጭት (Transmission Line) መስመር እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ጥናት ማካሄድ፣
 • የ25 መለስተኛ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ፣
 • የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች የዕቃ ግዥና ግንባታ፣
 • የቧንቧና መገጣጠሚያ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ውኃ ማጠራቀሚያ ጋን ግዥ፣
 • የማጠራቀሚያ ጋን እና ሌሎች አስፈላጊ የህንጻ ግንባታ ሥራዎች፣
 • የዋና መስመር እና የሥርጭት መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
 • የፓምፕና ጥበቃ ቤት ግንባታ እንዲሁም የትራንስፎርመር ተከላ ሥራ
 • የግንባታ ሱፐርቪዥን ሥራ
 • የመዳረሻ መንገድ ግንባታ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

 • በ2006 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

 • በ2009 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- በጥናት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለጊዜው ዋጋውን መገመት አልተቻለም፡፡

መግቢያ

በ2006 በጀት ዓመት በመንግስት በጀት 25 የመለስተኛ ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፈሮ ለማከናወን በዕቅድ ተይዟል፡፡ ጉድጓዶቹ በአዲስ አበባ አካባቢ የሚቆፈሩ ሲሆን ምርታቸውን በቀጥታ የነባር ማጠራቀሚያዎች አልያም አዲስ ወደ ሚገቡ ማጠራቀሚያዎች የሚሰባሰቡ ይሆናል፡፡ የኘሮጀክቱ ሥራ ተጠናቆ ውሃው ወደ ተዘጋጀለት ማጠራቀሚያ ሲገባ በምርት ከ 85,000 በላይ የሚሆን ሕዝብ በቀን 110 ሊትር እንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡

የኘሮጀክቱ አስፈላጊነት

የአዲስ አበባ ሕዝብን የእለት ተእለት የውሃ ጥያቄ ቀስ በቀስ ለመፍታትና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሣደግ መንግሥት ከፍተኛ መዋለ ንዋይ እያፈሰሰ ይገኛል፡፡ በተለይ ከውሃ መገኛ ቦታዎች ርቀው የሚገኙ የከተማው አካባቢዎች ማለትም ኮንደሚኒየም ቤቶች ያለውን የውሃ ፍላጐት ለማሟላት እነዚህ 20 ጉድጓዶች ከፍተኛ ጥቅም አላቸው፡፡

የኘሮጀክቱ ዓላማ

በ2007/08 በጀት ዓመት የጉድጓድ ቁፋሯቸው የውሃ ጥራታቸው የተጠናቀቀላቸውን 25 ጉድጓዶች በቀጥታ ወደ መስመር በማስገባት ለከተማው ለዋሪ የተሻለ ጥራቱን የጠበቀና በስርጭቱ ስፋት የተሻለ አገልግሎት መስጠት፣

የኘሮጀክቱ ግብ

በተለዩ የውኃ መገኛ አካባቢዎች የ25 መለስተኛ ጉድጓዶች ቁፋሮና ተያያዥ ሥራዎች ይጠናቀቃል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

የተቆፈሩት ጉድጓዶች ወደ አገልግሎት መግባት ተጨማሪ ውሃ ወደ ሲስተም ውስጥ እንዲገባ ስለሚያደርግ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያለውን ሕብረተሰብ/ኮንደሚኒየም አካባቢዎች) ጨምሮ በተራዘመ የጊዜ ሰሌዳ የውሃ ስርጭት የሚያገኘውን ሕዝብ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 • ከ20 ጉድጓዶች ውስጥ የቀሪ 8 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ማከናወን፣
 • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም ለተጨማሪ 5 ጉድጓዶች የጂኦፊዚካል ጥናት እና የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን፣
 • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የተጨማሪ 5 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ማከናወን
 • የውኃ ቧንቧና መገጣጠሚያ አቅርቦት ሥራ ማጠናቀቅ
 • [1]የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም ለ6 ጉድጓዶች የሲቪል ሥራ (የጥበቃ ቤት፤ መቆጣጠሪያ ቤት፤ አጥር እና ሽንት ቤት) ማከናወን፣
 • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም ለጉድጓዶች የሲቪል ግንባታ ሥራ የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን፣
 • ለተቆፈሩ የውኃ ጉድጓዶች የኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት፣

የአፈጻጸም ስልቶች

የ25 ጉድጓዶች ቁፍሮ ሥራ በታለመለት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የሚከተሉት የአፈጻጸም ስልቶች አስፈላጊ ይሆናሉ፡፡

 • በቁፋሮ ሥራ የሚሳተፉ ተቋራጮች የሚያቀርቡትን ሰነድ መገምገም፣
 • ለቁፋሮ የሚመረጡ ተቋራጮችን መቆጣጠር፣
 • የሥራ ሣምንታዊና መርሃዊ ሪፖርቶችን መቆጣጠርና መገምገም፣

የአካባቢና ማህበራዊ ትንታኔ

የቁፍሮ ሥራ በአብዛኛው በማህበራዊ ጉዳይ የሚኖራቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ከቦታ ይገባኛል ጥያቄ እና ከካሣ ክፍያ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በአካባቢያቸው የሚገኘው ቀበሌና ክ/ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መስራት ይገባቸዋል፡፡ በሥራው በተለይ የጉድጓዶቹን አካባቢ ነዋሪ የመጀመሪያ ተጠቃሚ ስለሚያደርገው ችግሩን ለማቅለል ይሞከራል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርዓት

የሚሰሩትን ዝርዝር ሥራዎች ለመቆጣጠር የተዘረዘሩትን የክትትል የግምገማ ሥርዓቶች መካከል፣

ሀ/    ለቁፋሮ ሥራ የሚመረጡ የሀገር ውስጥ ተቋራጮች በሚያስገቡት ሰነድ ከፍላጐት ጋርና የገበያውን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ መሆኑ ይመዘናል፣

ለ/    በቁፋሮ ወቅት ከኘሮጀክት ቢሮው በተመደቡ ባለሙያዎች የሥራውን ጥራትና መስፈርት በተዘጋጀው ውለታ መሠረት ይታያሉ፣

ሐ/    ለተሰሩት ሥራዎች የሚቀርቡ ማናቸውም ክፍያዎች በቅድሚያ በሚደረጉ ማጣራቶች ተመዝነው ክፍያቸው የሚፈፀምበት ሥርዓት ይተገበራል፣

ስጋትና ምቹ ሁኔታዎች

የኘሮጀክቱ ሥራ በታሰበለት ፍጥነትና በታሰበበት የጊዜ ገደብ ለመወጣት ስጋት ሆነው የሚቀጥሎ ጉዳዮች፡

 • ለቁፋሮ የሚሆኑ ግብዓቶች በታሰበላቸው የጊዜ ገደብ አለመገኘት፣
 • የይዞታ ይገባኛል ጥያቄ ችግር፣

ምቹ ሁኔታዎች

 • የውሃ ጥያቄ ከፍተኛ መሆን፣
ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
5 በተለያዩ የኮንዶሚኒየም ግንባታ በሚከናወንባቸው ቦታዎች የመለስተኛ ጉድጓዶች ቁፋሮ ፕሮጀክት   65,466,996 65,466,996 0 0 0
5.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ20 መለስተኛ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ማከናወን 174,655,089 30,000,000 30,000,000 በተገባው ውል ስምምነት መሠረት ለ12 ጉድጓዶች ለሚከፈል ቀሪ ክፍያ ብር 16.9 ሚሊየን እንዲሁም አዲስ ለ4 ጉድጓዶች ለሚገባ ውለታ ብር 45.9 ሚሊየን ብር ተደምሮ አጠቃላይ በጀቱ ተይዟል
5.2 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የተጨማሪ 5 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ማከናወን 50,000,000 15,000,000 15,000,000 በሚገባው ውለታ መሠረት በበጀት ዓመቱ ለሚቆፈሩ 5 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ የተያዘ በጀት ነው፡፡
5.3 የውኃ ቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ መፈጸም 11,171,490 4,438,236 4,438,236 ከዕቃ አቅርቦቱ ጋር በተያያዘ በ2008 በጀት ዓመት ለሚከፈል የፍራት 2.1 ሚሊየን ብር እና ቀሪ የገንዘብ ክፍያ የተጠቀሰው ብር ተይዟል
5.4 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም ለ20 ጉድጓዶች የሲቪል ሥራዎች (የጥበቃ ቤት፤ መቆጣጠሪያ ቤት፤ አጥር እና ሽንት ቤት) ማከናወን 15,000,000 10,000,000 10,000,000 ለሲቪል ሥራው የቅድመ ክፍያ እና ለጉድጓዶች ለሚጠናቀቅ ሥራ የተያዘ በጀት ነው፡፡
5.5 ለተቆፈሩ የውኃ ጉድጓዶች የኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት 17,000,000 5,000,000 5,000,000 ከዚህ ቀደም ለ70ሺህ ውኃ አቅርቦት ለጉድጓድ ትራነስፎርመር አቅርቦት የተያዘውን በጀት መነሻ በማድረግ እነዚህ ጉድጓዶች የሚፈልጉት ትራንሰፎርመር አቅም አነስተኛ እንደሚሆን ግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ ፕሮጀክት ለተቆፈሩ 20 ጉድጓዶች ትራንሰፎርመር አቅርቦት በጀቱ ተይዟል
5.6 ለቁፋሮ ሥራ የሱፐርቪዥን ክፍያ ሥራ 4,186,391 278,760 278,760 በተገባው ውል መሠረት ለሱፐርቪዥን ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡
5.7 ለጉድጓዶች የሲቪል ግንባታ ሥራ የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን፣ 600,000 600,000 600,000 በሚገባው ውለታ መሠረት ለ6 ወር ሥራ ለሚውል የሱፐርቪዥን ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡
5.8 የካሳ ክፍያ መፈጸም 150,000 150,000 150,000 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡