ዳይሬክተሯ ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የሂሳብ መዝጋት እና ኦዲት ስራ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

ባለስልጣኑ አሁን እየሰራ ያለውን ስራ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራአስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ አጭር ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ባለስልጣኑ እየሰጠ ስላለው የአቅም ግንባታ ስልጠና እና እያመጣ ያለውን ለውጥ በተመለከተም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ዳሬክተሯ ጄኒፈር ጄ ሳራ በበኩላቸው አሁን እየተሰራ ባለው ስራ መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ባለስልጣኑ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ በተለይም በፍሳሽ ቆሻሻ አጣርቶ ማስወገድ እና መልሶ መጠቀም ፣በአቅም ግንባታ ስራ ፣በተፋሰስ ልማት ፣ በሂሳብ አስተዳደር እና መሰል ስራዎች ላይ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡