አባላቱ በባለሥልጣኑ የለገዳዲ ግድብ ማጣሪያ ጣቢያን ዛሬ የጎበኙ ሲሆን በየቤታችን በመስመር የሚሰራጨው ውሃ በጣም ብዙ ጉልበትና ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበት የሚመረትና የሚሰራጭ መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል።
አክለውም ከምግብ ማብሰልና ከመጠጥ ፍጆታ ባለፈ ለአረንጓዴ ልማት በተለይም ደግሞ ለግንባታና ለተሽከርካሪዎች ማጠቢያ ለሚውለው ንጹህ የመጠጥ ውሃ ሌሎች አማራጮች ቢፈለግ የሚል አስተያየትም ሰጥተዋል።
ደንበኞቹ ከዚህ በኋላ ጠብታ ውሃ እንኳን ሲባክን በቸልታ እንደማያልፉ ገልጸው፤ በየቤታችን በመስመር የሚደርሰውን ውሃ በቁጠባ መጠቀምና ለልጆቻችን ማቆየት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
ጎብኝዎቹ ከአራት ክ/ከተማ እና ከ18 ወረዳዎች የተውጣጡ ሲሆን፤ በግድቡ ውሃ ተመርቶ ሲሰራጭ የሚያልፍባቸውን ሂደቶች የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።
Recent Comments