ከፊታችን የካተቲ ስምንት እስከ አስራ ሁለት ድረስ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና የሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡ ይህ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ባለሥልጣኑ በዘጠኙም ቅ/ጽ/ቤቶችና በዋና መ/ቤት 24 ሰዓት በተጠንቀቅ የሚሰራ ኮሚቴ አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

ባለሥልጣኑ ለእንግዶች ማረፊያ ለተዘጋጁ 143 ሆቴሎች፣ የስብሰባ አዳራሽ እና 28 ኤምባሲዎች አስፈላጊዉን አገልግሎት ለመስጠት በተመረጡት ቦታዎች ፍተሻ በማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የዋና ዋና የውሃ መስመሮች፣ የሪዘርቫየሮች እና ቫልቮች ፍተሻም ተደርጓል፡፡ እንዲሁም 12 አማራጭ የውሃ ቦቴዎችን በማዘጋጀት እና የአስቸኳይ ጊዜ ዕቅድ በመንደፍ በመጠባቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ባለፈም ከሌሎች የመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ስራዎችን የጋራ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡