የአዲስ አበባ ወሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አለም አቀፍ የአረንጓዴ እድገት ኢንስቲቲዩት (GGGI) ባዘጋጀው ኢግዚብሽን ላይ በወሃ መገኛ አካባቢዎች እየሰራ ያለውን የተፋሰስ ልማት ስራ ማቅረቡ ይታወቃል ::ዛሬ በእግዚብሽኑ መዝጊያ ላይ ባለስልጣኑ እየሠራቸው ባሉ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች 2022 ምርጥ ብሔራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣም ሻምፒዮን ሆኖ የዋንጫ እና ምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶለታል፡