ባለስልጣኑ የፍሳሽ ቆሻሻ የማንሳት አገልግሎቱን በላቀ ደረጃ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ከአለም ባንክ በተገኘ 15 ሚሊዮን ዶላር ብድር ተሸከርካሪዎችን አስገብቷል፡፡

ባለስልጣኑ ዘመናዊ የፍሳሽ በመስመር ማስወገድ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የከተማችን ነዋረዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ነው ተሸከርካሪዎችን ያስገባው ፡፡

ተሸከርካሪዎቹን ስራ ለማስጀመር በተዘጋጀ ስልጠና ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራአስኪያጅ ኢ/ር ዘሪሁን አባተ አዲሶቹ ተሽከርካሪዎች በአማካኝ የሚነሳውን የፍሳሽ መጠን ከማሳደግ ጎን ለጎን በወረፋ ምክኒያት መስተናገድ ያልቻሉ ደንበኞችን ችግር ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡

ባለሙያዎችም የሚያገኙትን ስልጠና ከቀም ሲል ከነበራቸው ልምድ እና እውቀት ጋር በማቀናጀት ተሸከርካሪዎቹ ያለ ችግር ረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ የድሻቻን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ተሽከርካሪዎችን ያቀረበው ሎንጎ የተሰኘ የጣሊያን ኩባኒያ G6 ትሬዲንግ ከተባለ አገር በቀል ኩባኒያ ጋር በመተባበር ከተሸከርካሪዎቹ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን ባለሙያዎች ዛሬ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

አቅራቢ ኩባኒያው በስራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል የቴክኒክ ስልጠና ከባለስልጣኑ ጋራጅ እና ከአፕሬተሮች ለተውጣጡ ባለሙያዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡