የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን የጎበኙት የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደንበኞች ፎረም ተወካዮች በፍሳሽ ቆሻሻ ማንሳት፣ ማጣራት እና ማስወገድ ላይ በቂ ግንዛቤ ማግኘታችውንና በአከባቢያቸው በግንዛቤ እጥረት ምክንያት በመፀዳጃ ቤት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ከጎብኝዎች መካከል እስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ይድነቃቸው አስራቱ ከየቤቱ የሚነሳው ፍሳሽ ቆሻሻ ሜዳ ላይ የሚደፋ ሳይሆን ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበት የሚጣራ እና አከባቢን በማይበክል መልኩ የሚለቀቅ መሆኑ እንዳስደሰታቸው ገልፀው ቁርጥራጭ እና ጠጣር ነገሮችን ወደ መፀዳጃ ቤቶች የመጣል ተግባር ፍሳሽ ቆሻሻ የማጣራቱን ሂደት ስለሚያስተጋጉል መቆም አለበት ብለዋል።

ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ነዋሪዎችን ወክላ የተገኘችው ወ/ሮ ማሜ ቦጋለ በበኩላቸው”ፍሳሽ ቆሻሻ ማንሻ መኪና ያነሳዋል በሚል ግምት የፅዳት መጠቀሚያ እቃዎችን እና ባዕድ ነገሮችን ወደ መፀዳጃ ቤት እንጥል ነበር፤ እነዚህ ቁሳቁሶች የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያውን ስራ ሲያውኩ ማየቴ ስለተሰማኝ ከዚህ ቡሃላ ከራሴ ጀምሮ ሌሎችም እንዲጠነቀቁ አስተምራለሁ” ብለዋል ።

የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በቀን 100 ሺህ ሜትር ኪውብ ፍሳሽ ቆሻሻ የማጣራት አቅም ያለው ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ነው።