የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ለ25,478 አበወራዎች የፍሳሽ መስመር ቅጥያ በማከናወን ዘመናዊ የፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጡ ተገለፀ፣

በመንፈቅ-ዓመቱ ለ14,385 አባወራዎች የፍሳሽ መስመር ለመቀጠል ታቅዶ ለ25,478 አባወራዎች ቅጥያ በማከናወን የፍሳሽ መስመር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በ2017 የመጀመርያው ግማሽ ዓመት የተከናወነው የፍሳሽ መስመር ቅጥያ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ15,860 ብልጫ አሳይቷል፡፡