የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣንም ቀኑን በማስመልከት ፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ አጣርቶ የማስወገድ አገልግሎት ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገልጸል፡፡
ባለሥልጣኑ አሁን ያለው ፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ የማጣራት አቅም በቀን 148 ሺህ ሜ.ኩብ ማድረስ ችሏል፡፡
በዘመናዊ መንገድ ፍሳሽ ሰብስቦ የማጣራት አቅሙ ከፍ ያደረጉት በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የቃሊቲ ፣ የኮተቤ ፣ ሚኪላንድ፣ ገላን እንዲሁም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መሰረት አድርገው የተሰሩ 12 ያልተማከሉ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ናቸው ፡፡
ባለስልጣኑ እስካሁን 172‚000 የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ያሉት ሲሆን በዚህ በጀት አመት 72‚000 አዲስ የቤት ለቤት ቅጥያ ለማከናወን አቅዶ እየሰራ ነው፡፡
በአሁን ሰዓት በቀን 88‚000 ሜ.ኪ ፍሳሽ ቆሻሻ እያጣራ ይገኛል፡፡ ይህን ቁጥር በተያዘው በጀት አመት አዳዲስ ቅጥያ በመፈጸም ወደ 98 ሺህ ሜ.ኩብ ከፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
በዚህ በጀት አመት ዘመናዊ የፍሳሽ አወጋገድ ተጠቃሚ ከሚሆኑ 72‚000 ደንበኞች መካከል 60 በመቶ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲሆኑ ሌሎች 40 በመቶዎቹ ደግሞ የተለያዩ የከተማዋ ነዋሪዎች ናቸው፡፡
ባለስልጣኑ ጽዱ እና ውብ አዲስ አበባን ለመፍጠር የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ማዘመን ፤ መሰረተ ልማቶቹ በተስፋፉበት አካባቢ የቤት ለቤት ቅጥያ መፈጸም ከህብረተሰቡ የሚጠበቅ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
የዘረፉ ትልቅ ተግዳሮት የሆነውን የማንሆል ክዳን ስርቆት እና ባእድ ቆሻሻ በፍሳሽ መስመር መጨመር ህብረተሰቡ እንዲከላከልም ጥሪ ቀርቧል፡፡