ማጣሪያ ጣቢያው ሲመሰረት የነበረውን በቀን 7ሺ500 ሜ.ኩ የማጣራት አቅም ወደ 100ሺ ሜ.ኩ እንዲያድግ ተደርጎ ወደ ስራ የገባው ባሳለፍነው ሰኔ 30 /2010 ዓ.ም ነበር፡፡

ባለስልጣኑም በዚህ በጀት አመት ጣቢያው ሲመረቅ ከነበረው የማጣራ አቅም ወደ 25 ሺ ሜ.ኩ ለማሳግ እቅድ የያዘ ሲሆን በበጀት አመቱ አጋማሽ 40ሺ ሜ.ኩ ማድረስ ችሏል፡፡ይህም ትልቅ ውጤት ነው ያሉት የባስልጣኑ የፍሳሽ ደንበኞች ቅጥያ ንኡስ የስራ ሂደት መሪ  አቶ ዘላለም ከተማ ፤ለፕሮጀክቱ  ከተከናውኑት ዋና ዋና ተግባራ መካከል  230 ኪ.ሜ መለስተኛ እና የቤት ለቤት ቅጥያ ተቀባይ መስመሮች በለቡ፣ በቤቴል፣ በአየር ጤና፣ በአለም ባንክ፣ በዘነበ ወርቅ፣ ቆሬ፣ ጀሞ፣ ፕላን ኢትዮጵያ፣ 53 ቀበሌ፣ ዘንባባ ሆስፒታል፣ ሳሪስ አዲሱ ሰፈር፣ ጎፋና አንበሳ ጋራዥ እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች ላይ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ መከናወኑን ገልጸዋል ፡፡

የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ዋና ፍሳሽ ማስተላለፊያ 18 ኪሎ ሜትር እና  28 ኪሎ ሜትር ትራንክ ላይን ፣ የ 80 ኪሎ ሜትር መለስተኛ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ እና የ 4 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ መስመር ማገናኘት ሥራ በአሁኑ ጊዜ  98 በመቶ መጠናቀቁን ጠቁመዋል  ፡፡

ፕሮጀክቱ በ2ቢሊዮን ብር በጀት እተሰራ ያለ ሲሆን 1.5 ሚሊየን የሚጠጉ የከተማዋ ነዋሪዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ያደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፍሻሽ መስመር የደረሰበት አካባቢ ነዋሪዎችም በህጋዊ መንገድ በማገናኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ባለስልጣኑ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡