የኘሮጀክቱ ሥም፡    የአቃቂ አካባቢ ፍሳሽ ማጣሪያና የፍሳሽ መስመር ጥናት  

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ቦሌ ቡልቡላ ቦሌ ሚካኤል ወዘተ… ሆኖ ዋና የፍሣሽ መስመሮቹ የሚገነቡ ወይም በመገንባት ላይ ያሉ በአካባቢው የሚገኙ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ያካትታል፡፡

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ቦሌ ቡልቡላ ቦሌ ሚካኤል እና አዲስ የሚገነቡትን የኮንዶሚኒየም ቤቶች እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎችን የፍሣሽ አገልግሎት እንዲዳረስ መድረግ፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-በፍሳሽ ማስተር ፕላኑ መሠረት በአቃቂ አካባቢ የፍሳሽ ማጣሪያ እስከ 2007 በመገንባት በአካባቢው ለሚገኙ የኮንደሚኒየም ቤቶችና ቦሌ ሚካኤል.፣ ቦሌ ቡልቡላ እንዲሁም በርታ ሪል እስቴት አካባቢ ለሚኖሩ ወደ 500,000 ለሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 • ለ CHEFE SUB-CATCHMENT እና ለ AKAKI SUB-CATCHMENT የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
 • ለ CHEFE SUB-CATCHMENT እና ለ AKAKI SUB-CATCHMENT የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ሥራ፣
 • የግንባታ ቁጥጥር ሱፐርቪዥን ሥራ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

 • በ2003 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

 • በ2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 536,019,416 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

 መግቢያ

 የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን እ.አ.አ በ2ዐዐ2 ዓ.ም የአዲስ አበባን ፍሣሽ ማስተር ኘላን ክለሳ ማስጠናቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ማስተር ኘላን

ኘሮጀክቱ ሁለት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል፡፡ እነዚህም፡

ሀ/ የአቃቂ አካባቢ የፍሣሽ መስመር ግንባታ እና

ለ/ የአቃቂ አካባቢ የፍሣሽ ማጣሪያ ግንባታዎች ናቸው፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

የአቃቂ አካባቢ በከተማችን በከፍተኛ ፍጥነት እድገት በማሣየት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም አካባቢው ምንም አይነት የፍሣሽ ማስወገጃ መስመርና የፍሣሽ ማጣሪያ መስመር አልተገነባለትም፡፡

በአካበቢው በአሁኑ ጊዜ ከ150 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንዱስትሪዎች፣ ሪል ስቴቶች እና ሌሎችም የልማት ተቋማት ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡

ከእነዚህም የልማትና የሰፈራ ኘሮግራሞች ጋር የተያያዘ ከፍተኛ የሆነ የፍሣሽ ማስወገጃ ፍላጐቶች ከሕብረተሰቡ ቀርበዋል፡፡ እንደሚታወቀው የአ.አ.ው.ፍ.ባ አላማም የሕብረተሰቡን የፍሣሽ ማስወገጃ ጥያቄዎች ማስተናገድ እንደመሆኑ ይህንን ኘሮጀክት ቀርጾ አቅርቧል፡፡

የዚህ ሥራ ተግባራዊ መሆንም እ.ኤ.አ እስከ 2ዐ25 የሚኖረውን ፍሣሽ ማስወገድ ፍላጐት ምላሽ ይሰጣል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

የአቃቂ አካባቢ ፍሣሽ በአካባቢና ጤና ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የፍሣሽ መሰብሰቢያ መስመሮችን እና የፍሣሽ ማጣሪያ ኘላንት እንዲገነባ ማድረግ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

ኘሮጀክቱ በዋና ዓላማው ላይ መሠረት ያደረገ ግብ ይኖረዋል፡፡ ይኸውም የፍሣሽ መሰብሰቢያ መስመሮችና የማጣሪያ ኘላንት እንዲገነባ በማድረግ ፍሳሹ በአካባቢና በጤና ላይ የሚያስከትለውን ብክለት ማስወገድ ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች 

ሥራውን ተግባራዊ ለማድረግ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓት እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል፡፡ በዚህም፡

 • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
 • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
 • የአካባቢ ብክለትን ማስወገድና የተሟላ ጤና እንዲኖር ያደርጋል፡፡
 • የፀዳች አዲስ አበባ ብሎም ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ እድገት የተመቸች ከተማ እንድትኖረን ያደርጋል፡፡
 • ተጨማሪ የመስኖ ሥራዎችን ለመስራት የተጣራውን ፍሣሽ ለአካባቢው ግብርና እንዲውል ማድረግ ይቻላል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

 • በሁሉም ዩኒቶች የኤሌክትሮሜካኒካል እንዲሁም የመስመር ማገናኘት ስራን ማጠናቀቅ፣
 • ቀሪ 40 በመቶ የማድረቂያ መደብ ቁፋሮ እና ሙሌት ስራ ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ፣
 • የቀሪ 4 ኪ.ሜ ዝርጋታ ስራ በማከናወን የ22 ኪ.ሜ ዝርጋታ ስራ ማጠናቀቅ፣
 • ቃሊቲ ማረሚያ፣ ቦሌ ቡልቡላን ጨምሮ 4 የኮንደሚኒየም ሳይቶች አካባቢ የ4 ኪ.ሜ የመለስተኛ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራ ማከናወን

የክትትልና ግምገማ ሥርዓት

ከአማካሪው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥናቱን በሚገመግሙ ባለሙያዎች እየታዩ መዳበር የሚገባቸው ነጥቦች እንዲዳብሩ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የክትትል መመዘኛ ነጥቦችን በጨረታና በስምምነት ሰነዶች ላይ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡

ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች

ፕሮጀክቱን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃሉ፡

ሀ/ ሥጋቶች

 • የባለሙያ እጥረት
 • የባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን ያለመወጣት ችግር ናቸው፡፡

ለ/ ምቹ ሁኔታዎች

 • ሥራውን ተግባራዊ ለማድርግ የመንግስት ቁርጠኝነት
 • በሕብረተሰቡ በካል ያለው የውሃ ፍላጐት የናረ መሆኑ
 • በአካባቢው ያለው የኢንቨስትመንትና ልማት መስፋፋት
 • በአካባቢው የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት፤ ዘመናዊ የፍሳሽ መሰብሰቢያ እና ማጣሪያ ኘላንት የሚፈልጉ መሆናቸው
 • ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች

ከላይ ለተጠቀሱት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገው ጠቅላላ በጀት 71,703,391 ብር ሲሆን ዝርዝሩም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
11 የአቃቂ አካባቢ ፍሳሽ ማጣሪያና የፍሳሽ መስመር ጥናትና ግንባታ ፕሮጀክት   71,703,391 71,703,391 0 0 0
11.1 የጨፌ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታና ተያያዥ ሥራዎች ማከናወን 111,934,879 50,000,000 50,000,000 የዚህ የማጣሪያ ጣቢያ ግንባታን በተመለከተ ከተቋራጩ ጋር በነበረው የኮንትራት አስተዳደር ችግር አብዛኛው ክፍያ ያልተፈፀመ በመሆኑ ለቀጣዩ የበጀት አመት እንደሚተላለፍ ታሳቢ በማድረግ የተያዘ በጀት ነው፡፡
11.2 ከ22 ኪ.ሜ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ውስጥ የቀሪ 4 ኪ.ሜ. ዝርጋታ ማከናወን 42,007,739 10,000,000 10,000,000 ››
11.3 4 ኪ.ሜ የመለስተኛ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራ ማከናወን 4,500,000 4,500,000 4,500,000 ከዚህ በፊት ለ27 ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ የተገባውን ውለታ መነሻ በማድረግ ለዚህ ሥራ የሚወጣው ገንዘብ እስከ 4.5 ሚሊየን ብር ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል፡፡
11.4 የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ 220,000 በወር 3,960,000 3,960,000 በ2007 በጀት ዓመት ለአማካሪው ከዚህ በፊት ያልተከፈለው የ8 ወር ክፍያ እና የቀጣይ 4 ወር ክፍያ እንደሚፈጸምለት እና ለቀጣይ 2008 ለ6 ወር ሥራ የሚከፈለው በጀት ተጠቃሎ እንዲያዝ ተደርጓል፡፡
11.5 የካሳ ክፍያ 3,243,391 3,243,391 3,243,391 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡