የአካባቢው ነዋሪዎችም መንገድ እንሰራለን በሚል የውሃ መስመሩን ሲበጣጥሱ እንዲያቆሙ ብንማጸናቸውም በቸልተኝነት መስመሩን በጣጥሰው ለከፋ የውሃ ችግር ዳርገውናል ብለዋል፡፡
በተለይም በዚህ ችግር ምክኒያት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ፣ሁለት እና አስራ ሶስት በተለምዶ ቴክኒክ እና ሞያ፣ ታፍ ኦይል ጀርባ፣አለም ባንክ ፣ አርሴማ፣ ብስራት ሰፈር ፣ ፕሮጀክት 12 ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከ25ሺኅ እስከ 30 ሺኅ ለሚገመት ነዋሪ ውሃ የሚሰራጭባቸው የውሃ መስመሮች በመበጣጠሳቸው ለነዋሪዎቹ ውሃ ማሰራጨት አልተቻለም፡፡
በአሁኑ ሰዓትም የውሃ መስመሮችን መልሶ ለመዘርጋት የሚያስችል የመንገድ ንድፍም ሆነ ደብዳቤ ከባለስልጣኑ ያልመጣ በመሆኑ ለጥገና አዳጋች መሆኑን እያሳወቅን የአዲስ አበባ መንገድች ባለስልጣን አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡