የአዲሰ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከመንግስት ባለድርሻ አካላት፣ ኮንትራተሮች፣ አማካሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር  በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ውይይት አካሄደ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ በመድረኩ ላይ ላቅ ያለ ና ደካማ አፈጻጸም ያሰመዘገቡ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን  ለይተው አቅርበዋል ፡፡

የተለዩትም 52 የውሃ ፕሮጀክቶች የሚገነቡ ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች ናቸው፡፡አብዛኞቹ መልካም አፈጻጸም ያሳዩ ሲሆን በተቃራኒው የተወስኑት ደግሞ ከሚጠበቀው በታች ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በውሃ ፕሮጀክቶች  ትግበራ ወቅትም በባለስልጣኑ  በኩል ያጋጠሙ  ከካሳ ክፍያ፣  ከወሰን ማስከበር  እና ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተያዙ ጉዳዮች ዋነኛ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡

ተሳታፊ ከነበሩት መካከል የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተሰፋዬ በሰጡት አስተያየት ድርጅታቸው ውጤታማ የሆኑ 37 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ማጎልበታቸውንና በዚህም ከባለስልጣኑ ጋር ጥሩ የስራ ግንኙነት መፈጠራቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ባለስልጣኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያለባቸውን ክፍተቶች በለው የገለጹት የግብዓት አቅርቦት ችግር እና የአሰተዳደራዊ ቢሮክራሲ መጓተቶች  መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በወይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ  በመወከል የተገኙት  አቶ ዘውዴ ቀጸላ የከተማው ነዋሪዎች  በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ለሚያነሷቸው ጥይቄዎች በአፈጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በፊት  በነበረው አካሄድ መቀጠል አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸው ደካማ አፈጻጸም ያስመዘገቡ የወሃ ፕሮጀክት ኮንትራክተሮችና አማካሪዎችን ከእንግዲህ በኃላ የከተማ አስተዳደሩ እንደማይታገስ ገልጸዋል፡፡