በለገዳዲ ተፋሰስ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በትብብር የሚሰራው የቪተንስ ኢቪደንስ አመራሮች ፣የሰነዳፋ ከተማ አስተዳር ከንቲባ እና የባስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ልማቱም በውሃ ተፋሰሶች ዙሪያ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ወደ ግድብ የሚገባ ጥሬ ውሃ እንዳይበከል መከላከልን አላማ ያደረገ ነው ፡፡

ቪተንስ ኢቪደንስ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ25 ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች እና ህዝብ በሚበዛባቸው አከባቢዎች 153 ክፍል መፀዳጃ ቤቶችን ገንብቷል፡፡

የቪተንስ ኢቪደንስ ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ማርኮ ስከውተን በሰንዳፋ ከተማ ሙዋለ ህፃናት እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መፀዳጃ ቤቶችን ትላንት በጎበኙበት ወቅት ድርጅታቸው ባሰራው መሰረተ ልማት መደሰተቸውን ገልጸው መጸዳጃ ቤቶቹን በተገቢው መንገድ በመጠቀም የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪ የባለስልጣኑን ማሠልጠኛ ማዕከል የጎበኙት ሚስተር ማርኮን ድጅታቸው የባለስልጣኑን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ በሚሰጠው የአመራርነት ስልጠና (FLL) ላይ ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ ከባለስልጣኑ እና የአከባቢው አመራሮች ጋር በመመካከር በርካታ ስዎችን ለመስራት አቅደው ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩም በዚሁ ወቅት ተብራርቷል ፡፡

የሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድጋፌ ጸጋዬ በበኩላቸው በተሰሩ መጸዳጃ ቤቶች መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ በትምህርት ቤቶች ለመማር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ህብረተሰቡን በማሳተፍ እና ከባለስልጣኑ ብሎም ቪተንስ ኢቪደንስ ጋር በመነጋገር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን