በውሃ ዘርፍ ልማት ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ተቋማት በየዓመቱ በድምቀት የማያከብሩት ሲሆን በበዓሉ ድርጅታቸውን ከማስተዋወቅ ባሻገር ህብረተሰቡ ስለውሃ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋት ጉልህ ሚና ይኖርዋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በዓሉ በዋናነት የሚመለከተው እንደመሆኑ ለህብረተሰቡ በውሃ አጠቃቀምና አያያዝ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዕለቱም ውሃ እና ተፈጥሮ ያለው መሰተጋብር አሰመልክቶ የመወያያ ሰንድ በማቀረብ የፓናል ውይይት ይካሄዳል፡፡እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር  የውሃ እና ሳንቴሽን ክበባት  የተቋቋመባቸው  50 ት/ቤቶች የተወጣጡ  አባላት እና የክበብ ተወካይ መምህራን የበላስልጣኑ የውሃ መገኛ ግድቦች እና ማጣሪያ ጣቢያዎች የሚጎበኙ ይሆናል ፡፡ ይህም የባለሥልጣኑ ደንበኞች ስለተቋሙም ሆነ ስለአጠቃላይ የውሃ አቅርቦት ሥራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡ በተማሪዎች ዘንድ ይህ ግንዛቤ መፈጠሩ ደግሞ የእውቀት ሽግግር ከማድረግ አንፃር ጠቀሜታ ስለሚኖረው ህብረተሰቡ ውሃን እንዳያባክን እና በቁጠባ እንዲቀጠም ከማድረግ አኳያ ፋይዳው የጐላ ነው፡፡ በተጨማሪም በባለስልጣን መ/ቤቱ የውሃ አቅርቦት ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ የውሃ ፕሮጀክቶች አስመልክቶ የአዳራሽ ፎቶ ኤግዝቤሽን የሚካሄድ ይሆናል፡፡