የህዝበ ሀብት በሆነው የፍሳሽ መሰረተ ልማት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ዛሬም ቀጥሏል ፡፡

በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ፣ መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ እስከ ቆሬ ድልድይ ፣ከቆሬ ድልድይ ወደ አላርት ሆስፒታል የሚወስዱ እንዲሁም ከብሄረጽጌ ላፍቶ ድልድይ እስከ አረቄ ፋብሪካ ለፍሳሽ መሰረተ ልማቱ ተብሎም የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በከፍተኛ ወጪ ያሰራቸው የመዳረሻ መንገዶችም የአፈር መድፊያ ሆነዋል፡፡

አፈሩን እየተደፋ ያለው ደግሞ በማህበር በተደራጁ ወጣቶች አማካኝነት ነው፡፡

ባስልጣኑም ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ አደራጁን፣ፈቃጁን እና ሌሎች በጉዳዩ ላይ ይመለከታቸዋል ያላቸውን አካላትን በደብዳቤም ሆነ በአካል ቢጠየቅም ዛሬም ድረስ መፍትሄ አልተበጀለት ፡፡

አምፎ ቤቴል ሪልስቴት አካባቢ እንዲሁ መንገዱ ከጥቅም ውጭ እየሆነ ነው፡፡

ባለስልጣኑ እያለማ ሌላው እያጠፋ እስከመቼ ይዘለቅ ይሆን ?

ከታች በማሳያነት ያስቀመጥነው ፎቶም መንገዱ ሲሰራ የነበረው ሁኔታ እና አሁን የሚገኝበትን ደረጃ የሚያሳይ ነው::

(የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን)