ለአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ደንበኞች በሙሉ

ባለስልጣኑ ከሀምሌ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የውሃ አገልግሎት ክፍያችሁን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በሚከተሉት አማራጮች   እንድትከፍሉ ያሳውቃል፡፡

  1. በባንኩ ቅርንጫፍ (Branch Service)

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በኩል በመስኮት አገልግሎት በአካል ተገኝተው ክፍያቸውን መፈፀም ያስችላቸዋል፡፡ ባንኩ በከተማዋ ውስጥ ከሦስት መቶ በላይ ቅርንጫፎች ያሉት በመሆኑ ተደራሽነቱ ሰፊ ነው፡፡

  1. ከቁጠባ ሂሳብ ተቀናሽ በሚደረግ ክፍያ

ይህ አማራጭ የባለስልጣኑ ደንበኞች የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ አካውንት ካላቸው ባንኩ የውሃ ሂሳባቸውን እየቀነሰ እንዲከፍልላቸው የሚደረግበት አሰራር ሲሆን፣ አካውንት ከሌላቸው አዲስ አካውንት መክፈት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ አሰራር በደንበኞቹ ሙሉ ፈቃደኝነት የሚተገበር ነው፡፡

  1. በሞባይል ባንኪንግ (CBE Birr)

ይህ የክፍያ ዓይነት በተንቀሳቃሽ ስልክ የሚደረግ ክፍያ (Mobile payment) እና በወኪል የሚደረግ ክፍያን (Agent) የሚካትት ሲሆን በንግድ ባንኩ ተቀማጭ ሂሳብ የሌላቸው ደንበኞች የተወሰነ ገንዘብ በማስቀመጥ ገንዘባቸው እስኪያልቅ ድረስ ተቀናሽ እየተደረገ የሚከፍሉበት አማራጭ ነው፡፡

  1. በኢንተርኔት ባንኪንግ አማካይነት የሚፈፀም ክፍያ

ይህ አማራጭ ደንበኛው የሞባይልና የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆን ያለበት ከመሆኑ በተጨማሪ በሂሳብ ደብተሩ (በአካውንቱ) ላይ ገንዘብ ሊኖረው ይገባል፡፡

ከነዚህ አገልግሎቶች መካከል ደንበኛው በአካል ተገኝቶ በመስኮት በኩል ክፍያውን ሲፈፅም ለባንኩ  ብር 2 (ሁለት ብር) ብቻ የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍል ሲሆን በተቀሩት አማራጮች ሲጠቀም ግን በነፃ አገልግሎቱን ያገኛል፡፡

                                  የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን