የኘሮጀክቱ ሥም፡    ለኮንዶሚኒየም ቤቶች የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የኮንደሚንየም ቤቶች ግንባታ የሚከናወንባቸው እንዲሁም ሌሎች ከቤቶች ልማት ኤጀንሲ ጋር በመነጋገር የሚወሰኑ ይሆናሉ፡፡

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡-ዘመናዊ የፍሳሽ አገልግሎት ያልተዳረሰባቸውን የኮንደሚኒየም ቤቶችና በአካባቢው የሚገኙ የህብረተሰብ ከፍሎችን የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ኘሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን አገልግሎት የሚሰጠው ለኮንዶሚኒየም ቤቶች ብቻ ሣይሆን በአካባቢው ለሚገኙ የልማት ተቋማትና ቤቶችም ጭምር ነው፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- በቂርቆስ ክ/ከተማ የሚገኙ ኮንደሚኒየም ቤቶች (ጠመንጃ ያዥ፣ አማልጋ ሜትድ፣ ቂርቆስ፣ 34 ሜዳ፣ መስቀል ፍላውር እና ማምረቻ ሳይቶች) የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ጺሆን፣ ሰሜን ማዘጋጃ፣ ፖሊስ ክበብ፣ ናይጄሪያ ኤንባሲና ቀጨኔ አካባቢ የሚገኙ የኮንደሚኒየም ቤቶች የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማጠናቀቅ፣
  • የፍሳሽ ቧንባና መገጣጠሚያ ግዥ
  • የማንሆል ክዳን ግዥ
  • 23 ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ማከናወን፣
  • 230 የመቆጣጠሪያ ሳጥን ግንባታ ማከናወን፣
  • 606 የቅጥያ መስመሮችን ማገናኘት፣
  • ከዚህ በፊት ከዚህ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ለተሰራ የፍሳሽ መስመር ሥራ ቀሪ ክፍያ መፈጸም፣

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2001 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2007 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 63,240,585 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን እ.ኤ.አ. በ 2ዐዐ2 ዓ.ም የአዲስ አበባን ፍሣሽ ማስተር ኘላን ክለሳ ማስጠናቱ ይታወቃል፡፡ ይህ የፍሣሽ ማስተር ኘላን ሁሉንም የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚያዳርስ በመሆኑ የዚህ ጥናት አስፈላጊነት ጉልህ ሆኖ ታይቷል፡፡ ስለሆነም በዚህ ማስተር ኘላን ጥናት ውስጥ ላልተካተቱ የከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ከቤቶች ለሚለቀቁ ፍሣሾች የማስወገጃ መስመሮች እና አነስተኛ ማጣሪዎች አስፈላጊ ሆነው ስለተገኙ በ 2ዐዐ3 የበጀት ዓመት በተመረጡ የኮንደሚኒየም ቤቶች የፍሳሽ መስመር ግንባታ የሚከናወን ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት እያደረጋቸው ካሉ ጥረቶች ውስጥ አንዱና ዋናው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ነው፡፡

መስተዳድሩ በከተማዋ በሁሉም ክ/ከተሞች ግንባታውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ በጉለሌ፣በቂርቆስ፣ በአራዳና በሌሎችም ክ/ከተሞች እና ጺሆን፣ ሰሜን ማዘጋጃ፣ ፖሊስ ክበብ፣ ናይጄሪያ ኤንባሲና ቀጨኔ አካባቢ የተገነቡ የኮንደሚኒየም ቤቶች በአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣና ማስተር ኘላን ውስጥ ያልተካተቱ ስለሆነ ለነዋሪዉ የፍሣሽ ማስወገጃ መስመሮችን ለመዘርጋት በተጨማሪም ማጣሪያ ለመገንባት የዚህ ኘሮጀክት መቀረጽ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

የዚህ ሥራ ተግባራዊ መሆንም እ.ኤ.አ እስከ 2020 የሚኖረውን ፍሣሽ ማስወገድ ፍላጐት ምላሽ ይሰጣል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

በተለያዩ ክ/ከተሞችና አካባቢዎች የተገነቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ሌሎች ድርጅቶች የፍሳሽ ማስወገጃ ችግር ያለባቸው በመሆኑ የፍሳሽ መሰብሰቢያ መስመሮችን እና የፍሳሽ ማጣሪያዎችን እንዲገነባ በማድረግ በአካባቢና በጤና ላይ የሚከሰተውን ችግር ማስቀረት ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

የፍሳሽ መሰብሰቢያ መስመሮችና የማጣሪያ ኘላንት እንዲገነባ በማድረግ ፍሳሹ በአካባቢና በጤና ላይ የሚያስከትለውን ብክለት ማስወገድ ነው፡፡ በዚህም ኮንዶሚኒየም ቤቶች ድርጅቶች እና መኖሪያ ቤቶች የፍሣሽ መስመሮቻቸውን የሚያገናኙበት ዋና የፍሣሽ መስመር እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በቂርቆስ ክ/ከተማ የሚገኙ ኮንደሚኒየም ቤቶችን (ጠመንጃ ያዥ አማልጋ ሜትድ፣ ቂርቆስ፣ 34 ሜዳ፣ መስቀል ፍላውር እና ማምረቻ ሳይቶች) የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ሥራው ተግባራዊ ሲሆን በኮንደሚኒየም ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ሚሆኑ ሲሆን በዚህም፡

  • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
  • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
  • የአካባቢ ብክለትን ማስወገድና የተሟላ ጤና እንዲኖር ያደርጋል፡፡
  • የፀዳች አዲስ አበባ እንድትኖረን ያደርጋል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የመጨረሻ እና የመያዥያ ክፍያ መፈጸም

የአፈጻጸም ስልቶች

  • አማካሪ መምረጥና አማካሪው ጥናቱን እንደያከናውን ማድረግ እና ሥራውን መከታተል፣
  • የመስመር ዝርጋታ ሥራ በዘርፉ ልምድ ላላቸው ተቋራጮች ለመስጠት በመመዘኛው መስፈርት መሠረት ተጫራቾች ይገመገማሉ፣ ለአሸናፊው ሥራው ይሰጣል፣

ፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • ሥራውን የሚያጠናና በግንባታም ወቅት ሥራውን የሚከታተል አማካሪ የሚመረጥ ሲሆን፣ አማካሪው የተጠየቀውን የሙያ አይነትና ባለሙያ በማቅረብ ጥናቱን ያከናውናል፡፡ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱም በኩልም እንዲሁ ሥራውን የሚከታተሉ መሃንዲሶች  ይመደባሉ፡፡
  • ሲሚንቶ
  • የመቆጣጠሪያ ሳጥን

የፕሮጀክቱ ግምገማ ሥርዓት

  • ከአማካሪው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥናቱን በሚገመግሙ ባለሙያዎች እየታዩ መዳበር የሚገባቸው ነጥቦች እንዲዳብሩ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የክትትል መመዘኛ ነጥቦችን በጨረታና በስምምነት ሰነዶች ላይ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡
  • በግንባታ ሥራ ወቅት አማካሪው በሚያቀርበው የሥራ ክትትል ስልት መሠረት እና ባለቤቱ በሚመድባቸው መሃንዲሶች የሥራ ሂደት ክትትል ያደርጋል፡፡

ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች

ፕሮጀክቱ ተግባራው በማድረግ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃሉ፡፡

ሀ/ ሥጋቶች

  • የወሰን ማስከበር ችግር ናቸው፡፡

ለ/ ምቹ ሁኔታዎች

  • ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድርግ የመንግስት ቁርጠኝነት፣
  • በአካከባቢው ያለው የኢንቨስትመንትና ልማት መስፋፋት፣
  • በአካባቢው የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት፤ ዘመናዊ የፍሳሽ መሰብሰቢያ እና ማጣሪያ ኘላንት የሚፈልጉ መሆናቸው፣
  • የነዋሪው ግንዛቤ እያደገ መምጣት፣

ከላይ ለተጠቀሱት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገው ጠቅላላ በጀት 3,338,554 ብር ሲሆን ዝርዝሩም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
49 ለኮንዶሚኒየም ቤቶች የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት   3,338,554 0 3,338,554 0 0
49.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም ጨፌ ክሮሲንግ፣ ካራማራ  ክሮሲንግ፣ ለቡ ክሮሲንግ፣ አፈንጮ በር ክሮሲንግ የፍሳሽ መስመር በድልድይ ማሻገር (River crossing)  የግንባታ ስራ ማከናወን 13,354,213 3,338,554 3,338,554 የግንባታ ስራው በዚህ 2007 በጀት ዓመት የሚጠናቀቀቅ ቢሆንም የመጨረሻው ዙር ክፍያ እና የ5 በመቶ የስራ መያዣ ክፍያ ለሚቀጥለው በጀት አመት እንደሚከፈል ታሳቢ በማድረግ በጀቱ እንዲያዝ ተደርጓል፡፡