የኘሮጀክቱ ሥም፡      ለውሃ ማምረቻ ጣቢያዎቸወ የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት እና ትግበራ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ ው.ፍ.ባለሥልጣን

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ስርጭት አስተማማኝ እና ያልተቆራረጠ ለማድረግ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-የከተማውን የውኃ ሥርጫት ሥርዓት ዘላቂና አስተማማኝ እንዲሁም ያልተቆራረጠ ለማድረግ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • ለውሃ ማምረቻ ጣቢያዎቹ የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት በማከናወን ለትግበራ ዝግጁ ማድረግ፣
  • የ14 ከፍተኛ ጀነሬቶሮች ግዥ ማከናወን

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ2007 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ2009 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 20,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

 

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በዋነኝነት ከገፀ ምድርና ከርሰ ምድረ የውኃ መገኛዎች የሚያመርተውን የመጠጥ ውሃ ለከተማዋ ህብረተሰብ በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህ የውኃ ማጣሪያ ጣቢያዎች የሚመረተው ውኃ በአብዛኛው በተለያዩ የግፍት መስጫ ጣቢያዎች በተተከሉ የከርሠ ምድርና የገጸ ምድር ጠላቂ ፓምፖች አማካኝነት ወደ ከተማው የሚደርስ ሲሆን እንዚህን ፓምፖች ለማንቀሳቀስም ከፍተኛ ኃይል ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ይጠቀማል፡፡ ሆኖም በከተማዋ ውስጥ ባለው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት የውኃ ሥርጭት ሥርዓቱ በየጊዜው በመስተጓጎል ላይ ይገኛል፡፡በመሆኑም ይህን ችግር በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ ውስጥ ለመቅረፍ በ2006 በጀት ዓመት መ/ቤቱ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ በዋና ዋና ማሰራጫ ጣቢያዎች ላይ የ14 ጀነሬተሮች ተከላ ሥራ ለማከናወን የሚያስችል የጀነሬተሮች ግዥ ለመፈጸም እንዲሁም በመካከለኛ ጊዜ ውስጥ ከኤሌክትሪክ ኃይል ውጪ ያሉ አማራጭ የኃይል ምንጮችን በማጥናት ለመተግበር ይህ ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡

የሥራው አስፈላጊነት

ይህ ኘሮጀክት ተፈጻሚ ሲሆን የከተማዋን የረዥም ጊዜ የውኃ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ አማራጭ የውኃ መገኛዎች በመለየት ወደ ትግበራ እንዲገባበት የሚያስችል ይሆናል፡፡

የሥራው ዓላማ

የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ስርጭት አስተማማኝ እና ያልተቆራረጠ ለማድረግ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡

የሥራው ግብ

የከተማውን የውኃ ሥርጫት ሥርዓት ዘላቂና አስተማማኝ እንዲሁም ያልተቆራረጠ ለማድረግ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • ለውሃ ማምረቻ ጣቢያዎቸወ የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት፣
  • በዋና ዋና የውኃ ማሰራጫ ጣቢያዎች የተቆራረጠ የውኃ ሥርጫት በከተማዋ እንዳይፈገጠር የ14 ከፍተኛ ጀነሬተሮች አቅርቦት

በ2008 የሚከናወኑ ተግባራት

  • ቀሪ 80 በመቶ አማራጭ የውሃ አቅርቦት ምንጭ ጥናት ሥራ ማከናወን
  • የተቋራጭ ቅጥር ሂደት በመፈጸም አማራጭ የውሃ አቅርቦት ምንጭ ትግበራ ሥራ 15 በመቶ ማከናወን
  • የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን፣

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የዝርዝር ጥናት ዲዛይን ሥራ የሚያከናውን አማካሪ መቅጠርና የጥናት ሥራውን መከታተል፤
  • የዕቃ አቅርቦት ስራውን ለመፈጸም የሚያስችል የዕቃ አቅራቢ ቅጥር በመፈጸም የ14 ጀነሬተሮች ዕቃ አቅርቦት ሥራ መከታተል፣

ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • ዝርዝር ጥናቱን የሚያጠና አማካሪ የሚቀጠር ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን በሙሉ አማካሪ ድርጅቱ ያቀርባል፡፡
  • የዕቃ አቅርቦቱን የሚፈጽም ዕቃ አቅራቢ የሚቀጠር ሲሆን የዕቃ አቅርቦቱን በተፈለገው ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ አስፈላጊሁን ሁሉ በዕቃ አቅራቢው ድርጅት በኩል ይደረጋል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርአት

  • የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ለመከታተል ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርቶችን መከታተል፡፡
  • የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ በመገምገም እቅዱን መከለስ

በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/

ይህንን ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
33 ለውሃ ማምረቻ ጣቢያዎቸወ የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት እና ትግበራ ፕሮጀክት   6,657,165 0 6,657,165 0 0
33.1 ለውሃ ማምረቻ ጣቢያዎቹ የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት ሥራ ማከናወን 5,205,983 1,457,165 1,457,165 በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለጥናት ሥራው የሚከፈል በጀት ነው፡፡በተገባው ውለታ መሠረት ጥናቱ የ4 ወር ነው፡፡
33.2 የተቋራጭ/የዕቃ አቅራቢ ቅጥር መፈጸም የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ትግበራ ሥራ ማከናወን 5,000,000 5,000,000 5,000,000 በ2008 በጀት ዓመት በሚገባ ውለታ መሠረት ሥራውን ለማስጀመር የተያዘ በጀት ነው፡፡
33.3 የሱፐርቪዥን ሥራ ማከናወን 1,200,000 200,000 200,000 በሚገባው ውለታ መሠረት በወር 100ሺህ ብር ለመክፍል በ2008 በጀት ዓመት ለ2 ወር የሚከፍል በጀት ነው፡