የለገዳዲ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለገጣፌ ቄራ አካባቢ ባጋጠመው ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ባለ 700 ሚሊ ሜትር ከፍተኛ የውሃ መስመር ላይ የስብራት አደጋ አጋጥሟል፡፡በዚህም ምክንያት በተወሰኑ የከተማዋ አካባቢዎች የውሃ ሥርጭት ተቋርጧል፡፡

በቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም፣ በቦሌ አያት 1፣2፣3፣4 እና 5፣ በሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ በየካ አያት 1፣ 2 እና 3፣በየካ አባዶ ኮንዶሚኒየም እና በኮተቤ ገብርኤል በከፊል የሚገኙ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወደ መደበኛ ስርጭት ለማስገባት የጥገና ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡  ስለሆነም ደንበኞች አስከ ዓርብ ነሀሴ 18/2010 ዓ.ም ድረስ የጥገናው ስራ ተጠናቆ ወደ መደበኛ ስርጭት እስኪገባ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን እናሳውቃለን ፡፡