ገቢው የተሰበሰበው ከውሃ የአገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ልዩ ልዩ የገቢ ርዕሶች ነው፡፡
በባለሥልጣኑ ጥናት ዕቅድና በጀት ሃላፊ አቶ በዓለምላይ ባህሩ ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ 6ወራት 798 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የዕቅዱን 78 በመቶ ማሳካት ችሏል ብለዋል ፡፡
አፈጻጸሙ ከእቅዱ አንጻር ዝቅ ቢልም ከሀምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ13 ሚሊዩን ብር ብልጫ አሳይቷል ብለዋል ፡፡
በባለስልጣኑ በስድስት ወራት ከ96ሚሊዮን ብር በላይ ያልተሰበሰበ ውዝፍ ሂሳብ አለው፡፡ ከዚህም ውስጥ ከ50ሺኅ ብር በላይ ውዝፍ ያለባቸው 212 ደንበኞች መኖራቸውም ተመላክቷል፡፡
ባለስልጣኑ የዕለት ተዕለት ስራውን ለማከናወን በውስጥ ገቢ የሚንቀሳቀስ እንደመሆኑ የአገልግሎት ክፍያ የማይፈጽሙ ደንበኞች በስራው ላይ ትልቅ ተጽኖ እየፈጠሩ መኆኑን በመረዳት በአፋጣኝ ክፍያ እንዲፈጽሙ ያሳስባል፡፡