የኘሮጀክቱ ሥም፡         በአዲስ አበባ ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የሚወጣውን ዝቃጭ መልሶ መጠቀም ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች (አቃቂ፣ ኮተቤ ወዘተ…)

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- ከከተማዋ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች የሚወጣውን ዝቃጭ መልሶ ለመጠቀም የሚያስችል ሁኔታ እንዲፈጠር ማስቻል ነው፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-ከተለያዩ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ማለትም ከቃሊቲ፣ አቃቂ እና ኮተቤ የሚወጣውን ዝቃጭ መልሶ ለመጠቀም የሚያስችሉ አማራጭ ጥናቶችን በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የአማካሪ ቅጥር በመፈፀም የጥናት ሥራ ማከናወን

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ2007 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 8,500,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከከተማዋ የሚመነጨውን ፍሳሽ ቆሻሻ በፍሳሽ ተሸከርካሪ በዘመናዊ የፍሳሽ መስመር በመሰብሰብ በተለያዩ ማጣሪያ ጣቢያዎች በቃሊቲ፣ በአቃቂ እና በኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች በማሰባሰብ በአለም አቀፍ ስታንዳርድ መሠረት ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ አጣርቶ ያስውግዳል፡፡ ሆኖም ከፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ተጣርቶ የሚወጣውን ፍሳሽ መልሶ በመጠቀም ለተለያዩ አገልግሎቶች ለማዋል ያስችል ዘንድ የዚህ ፕሮጀክት መኖር አስፈላጊነቱ የማያጠያይቅ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በዚህ መነሻነት የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ይህ ጥናት አስጠንቶ ለትግበራ ዝግጁ ለማድረግ ያስችለው ዘንድ በ2007 በጀት ዓመት ይህን ፕሮጀክት ቀርጾ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

የሥራው አስፈላጊነት

ይህ ኘሮጀክት ተፈጻሚ ሲሆን የከተማዋን የተጣራ ፍሳሽ መልሶ ለመጠቀም የሚያስችል አማራጭ ጥናት በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ የሚያደርግ በመሆኑ የፕሮጀክቱ መቀረጽ አስፈላጊነት የማያጠያይቅ ይሆናል፡፡

የሥራው ዓላማ

ከከተማዋ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች የሚወጣውን ዝቃጭ መልሶ ለመጠቀም የሚያስችል ሁኔታ እንዲፈጠር ማስቻል ነው፡፡

የሥራው ግብ

ከተለያዩ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ማለትም ከቃሊቲ፣ አቃቂ እና ኮተቤ የሚወጣውን ዝቃጭ መልሶ ለመጠቀም የሚያስችሉ አማራጭ ጥናቶችን በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • ከተማዋን የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች የሚወጣውን ፍሳሽ መልሶ ለመጠቀም የሚያስችል አማራጭ የጥናት ሰነድ፣

በ2008 የሚከናወኑ ተግባራት

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን
  • በተጠናው ጥናት መነሻ ለትግበራ ሥራ የተቋራጭ ቅጥር መፈጸም፣

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የዝርዝር ጥናት ዲዛይን ሥራ የሚያከናውን አማካሪ መቅጠርና የጥናት ሥራውን መከታተል፤

ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • ዝርዝር ጥናቱን የሚያጠና አማካሪ የሚቀጠር ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን በሙሉ አማካሪ ድርጅቱ ያቀርባል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርአት

  • የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ለመከታተል ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርቶችን መከታተል፡፡
  • የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ በመገምገም እቅዱን መከለስ

በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/

ይህንን ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
30 በአዲስ አበባ ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የሚወጣውን ዝቃጭ መልሶ መጠቀም ፕሮጀክት   2,961,250 2,961,250 0 0 0
30.1 የአማካሪ ቅጥር በመፈፀም የጥናት ሥራ ማከናወን 8,500,000 2,961,250 2,961,250 በ2007 በጀት ዓመት የጥናት ስራውን ለማከናወን እንዲቻል በ8.5 ሚሊዮን ብር ውለታ የተገባ ሲሆን በተገባው ውለታ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት የሚከፈል በጀት ነው፡፡ አጠቃላይ የጥናት ሥራው 6 ወር የሚፈጅ ነው፡፡