ደንበኞቹ በየካ ፣በአራዳ እና በጉለሌ ክ/ከተማ ስር የሚገኙ 15 ንግድ ቤት ሆነው በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ሲከፍሉ የነበሩ ናቸው፡፡

ለዚህም ተግባራቸው ቅ/ጽ/ቤቱ የንግድ ፈቃዳቸውን በማየት አገልግሎት መስጠት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ኋላ በማስላት 47, 511, ብር እንዲከፍሉ ማድረጉን በቅ/ጽ/ቤቱ የውሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት መሪ አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሙሉጌታ አክለዉም ደንበኛች በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ለንግድ መጠቀም ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን አውቀው ለውጥ ሲያደርጉ ማሳወቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ህብረተሰቡም በመሰል ተግባር የተሰማሩ ደንበኞች ሲያጋጥሙት ለባለስልጣኑ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አስተላፈዋል፡፡

(በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን)