ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አከባቢዎች የተዘረጉ የውሃ መስመሮችን መረጃ ከመገኛ ቦታቸው ጋር (በGIS) ወደ ኮምፕውተር በማስገባት ነው የአገልግሎት ማሻሻያውን ማድረግ የቻለው፡፡

በቅርንጫፉ ደንበኞች አዲስ ውሃ ለማስገባት፣ መስመር ለማዛወር፣ የውሃ መስመር ለማሻሻል ግምት ለማሰራት እና ክፍያ ለመፈፀም ከ2 ጊዜ በላይ ምልልሶችን ማድረግ እንዲሁም አገልግሎቱን ለማግኘት ከ3-4 ቀን ወረፋ ይጠብቁ ነበር፡፡

ይህም ደንበኞች ካመለከቱበት ጊዜ ጀምሮ ቴክኒሻኖች በቦታው ተገኝተው ግምት የሚሰሩበትን፣ ደንበኛው ክፍያ የሚፈፅምበትን፣ ውል የሚያስሩበትን እና አገልግሎት የሚያገኝበትን ጊዜ ያጠቃልላል ፡፡

ሆኖም ግን የGIS ቴክኖሎጂን በመጠቀም በተደረገው የማሻሻያ ስራ ደንበኞች የሚያቀርቡትን ጥያቄ ከኮምፒውተር ላይ በማየት ብቻ ለግምት እና ለክፍያ የሚወስደውን ጊዜ ከግማሽ ቀን ባነሰ በማሳጠር ደንበኞች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የሠው ጉልበት፣ የነዳጅን እና የተሸከርካሪን ብክነት መቀነስ ተችሏል፡፡

ቅርንጫፉ የGIS ቴክኖሎጂን መጠቀሙ አገልግሎት አሠጣጡን እንዲያቀላጥፍ ከማስቻሉም ባሻገር መስመር ስብራት ሲያጋጥም ፈጥኖ ለማስተካከል እና ከኮምፒውተር በሚገኘው መረጃ መሰረት አስፈላጊውን የጥገና ግብዓት ለማዘጋጀት እንዳገዛቸው በቅርንጫፉ የውሃ ደንበኞች አገልግሎት ንዑስ የስራ ሂደት መሪ አቶ አቦማ ደፋልኝ ገልፀዋል፡፡