ማናጀሯ እና ልኡካቸው የለገዳዲ ግድብ ፣ በግድቦቹ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የተፋሰስ ልማት ስራ ፣ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት እና ማሰልጠኛ ተቋምን ነው የጎበኙት ::ጉብኝቱም በዋናነት አለም ባንክ ድጋፍ የሚያደረትግባቸውን ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ ማጤን እና ተጨማሪ ድጋፍ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡በቅርቡም በዓለም ባንክ ድጋፍ የለገዳዲና ድሬ ግድብ እድሳትና ማሻሻያ ለማከናወን ከዊ ቢውልድ (ሳሊኒ) ከተባለ የጣሊያኑ ኩባንያ ጋር የ11ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ስምምነት መፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡ማናጀሯም በተጨባጭ በግድቦቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ዛሬ የጎበኙ ሲሆን፤ በቀጣይ ባለስልጣኑ ድጋፍ የሚፈልግባቸው የገጸ-ምድር ውኃ ፕሮጀክቶች ላይ ለመመምክር ፍቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ከፍሳሽ ጋር በተያያዘ መልሶ መጠቀም ስራዎች ላይ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው በዚሁ ወቅት ተናግረዋል፡፡ ልኡካኑ ችግኝ የተከሉ ሲሆን ባስልጣኑ እየሰራ ያለውን የተፋሰስ ልማት ስራ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና ጥሩ እና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡