የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ብክነቱን በመስመር ሂደት የሚባክን (physical loss) እና ከውሃ ቆጣሪ ጋር የተያያዘ ብክነት (commercial loss) በመለየት የቁጥጥር ስራ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡የሚባክነውን ውሃ ማዳን የተቻለውም በመሣሪያ በመታገዝ ተከታታይነት ያለው የውሃ ብክነት ምርመራ እና ቁጥጥር (Active leak detection) ስራ በ305 ኪሎ ሜትር መለስተኛ የውሃ መስመር ላይ በመስራት 1,812 ቦታዎች ላይ የተገኘ ስብራት በመጠገን እና 11.68 ኪ.ሜ ያረጀ መለስተኛ የውሃ መስመሮችን እንዲሁም ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ ከ6,080 ቆጣሪዎችን በመቀየር ነው፡፡ ባጠቃላይ በ10 ወራት 625,272 ሜ.ኩብ ውሃ ማዳን የተቻለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 292,455 ሜትር ኪዩብ ከውሃ ቆጣሪ ጋር የተያያዘ ብክነት (commercial loss) መሆኑን በባለሥልጣኑ ገቢ የማይሰበሰብበት ውሃ ክትትል፣ ቁጥጥር እና አስተዳደር ንኡስ የስራ ሂደት ተወካይ አቶ ሃብታሙ ታደሰ አብራርተዋል፡፡ አቶ ሃብታሙ የውሃ ብክነት ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ተጠቃሚው ማበረሰብ የሚሰጠው ጥቆማ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ጠቁመው ይቨው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡