የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ (በመስመር) እና በተሽከርካሪ በማሰባሰብ ከ28 ሚሊዮን ሜ.ኩብ በላይ ፍሳሽ ቆሻሻ አጣርቶ አስወግዷል ።ባለስልጣኑ በዘመናዊ መንገድ ፍሳሽ የማሰባሰብ ስራን ከፍ ለማድረግም የ134.56 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ መስመር ጥናትና ዲዛይን ስራ ያጠናወቀቀ ሲሆን 82.41 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ መስመር ዝርጋታም አከናውኗል፡፡ ባለሥልጣኑ የፍሳሽ አገልግሎቱን ለማፋጠን ይረዳው ዘንድ ፍሳሽ ቆሻሻን በተሽከርካሪ የሚያሰባስቡ ተጨማሪ 90 ተሽከርካሪዎችን አስመጥቶ ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወሳል።