በጉባኤው ላይ ከመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ተቋሙ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተወሰዱ እርምጃዎችን የተመለከተ የሩብ ዓመት ሪፖረት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውሃ ስርጭት ፣ በዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ እና በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በገቢ አሰባሰብ ላይ በርካታ ደንበኞች የመክፈል ባህል ዝቅተኛ በመሆኑ በቅስቀሳ ሲያልፍም እርምጃ በመውሰድ የተቋሙን ገቢ አሰባሰብ ውጤታማ ለማድረግ መቻሉም በሪፖርቱ ላይ ተማላክቷል፡፡
የውሃ ስርጭቱን ለማሻሻል በኪስ ቦታዎች አፋጣኝ የውሃ ጉድጓድ የማልማት ስራ ከመስራት ጎን ለጎን የሚሰራጨው ውሃ ፍታዊ ለማድረግ የውሀ ፈረቃን የመከለስ እና የማሳወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
የዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር በተዘረጋባቸው አካባቢዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር በሩብ ዓመቱ ለበርካታ ደንበኞች የመስመር ዝርጋታ እና ቅጥያ ማከናወን መቻሉም በመድረኩ ተነስቷል፡፡
የፎረሙ አባላትም አለብን ያሉትን የውሃ መቆራረጥ ችግር ለመድረኩ ያቀረቡ ሲሆን በተመሣሣይ የተሰበረ መስመር ጥቆማ ሲደረግ ፈጣን ምላሽ አይሰጥም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡
በውይይት መድረኮቹ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ደንበኞችን ለማርካት ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውና የተነሱ ችግሮችም ከመሚለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር በመተባበር በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙ ይሰራል ተብሏል፡፡