በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኔ10-12 /2011 ዓ.ም በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተከበረ በሚገኘው የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በኢግዚብሽን በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

በስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ሲምፖዚየሙ እና ኢግዚብሽን  የኢፌድሪ ፕሬዝዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ከፍተውታል፡፡

በፕሮግራሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘርፋ ሙሁራን፣ በሀገር አቀፍ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፋ ላይ የተሰማሩ አካለት እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ እና አበዳሪ ተቋማት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በፕሮግራሙ ላይ ከፎቶ እና ከቪዲዮ በተጨማሪ የቃሊቲ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን እና የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ፍሳሽ ቆሻሻ የማጣራት ሂደት የሚያሳዩ ሞዴሎች ይዞ በመቅረብ የኮንፈረንሱን ተሳታፊዎች በማስጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡