የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዛሬ የ6 ወራት የመደበኛ  እና የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም በፕሮሰስ ካውንስል ገምግሟል ።

በግምገማው ወቅት ባለስልጣኑ ከገፀ ምድር እና ከርሰ ምድር  የወሃ መገኛዎች አለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ 94.2 ሚሊዮን ሜ. ኪ ወሃ አምርቶ ማስራጨት መቻሉ ተገልጿል ።

ይህም ከእቅዱ 82 % ሲሆን የእቅዱን ያክል ማሳካት ያልተቻለው በኤሌክትሮ ሜካኒካል ብልሽት፣ በኤሌትሪክ መቆራረጥ፣ ጉድጓዶች በጎርፍ መሞላት ዋነ ዋናዎች  ችግሮች ናቸው ።

ገቢን ከመሰብሰብ አንፃር በ6 ወራት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ  የሰበሰበ ሲሆን ይህም ከእቅዱ 96% ነው ።

ባለስልጣኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ይቻል ዘንድ ለሠራተኞች እየተሠጣ ያለው ስልጠና (FLL ) በተጨባጭ በጣም ጥሩ  ለውጥ እያመጣ መሆኑም በዚሁ ወቅት ተገልጿል  ።

ከስልጠና የወጡ ሠራተኞችም  የተለያዩ የፈጠራ ስራ በመሰራት ተቋሙን አያገዙት አንደሆነ በማሳያ ቀርቧል ::

በውይይቱ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ዘሪሁን አባተ
የተገኙ ጥሩ ውጤቶችን በማስቀጠል ፤ ክፍተቶችን ደግሞ ጠንክሮ በመሰራት ማሻሻል የሁሉም ሀላፊነት መሆኑ በመገንዘብ በትጋት መሰራት ያስፈልጋል ብለዋል።