ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የፋብሪካ ተረፈ ምርት በቦቴ ተሸከርካሪ በማጓጓዝ እና በባለስልጣኑ የፍሳሽ መስመር ውስጥ በመድፋታቸው ነው፡፡

በተደጋጋሚ በፍሳሽ መሰረተ ልማቱ ላይ የፋብሪካ ፍሳሽ ተረፈ ምርት በመደፋቱ የመዲናዋን ፍሳሽ አወጋገድ ዘመናዊ ለማድረግ በከፍተኛ ወጪ የተገነባው የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እና ባዮሎጂካል ክፍሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡

ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ባለስልጣኑ ለ24 ሰዓት ክትትል የሚያደርጉ ቡድኖችን በቋቋም ላለፍት 15 ተከታታይ ቀን እና ለሊት ክትትል አድርጓል ፡፡
በዚሁ መሰረት ጥር 24/2012 ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት በተለምዶ ጠማማው ፎቅ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ባእድ ፍሳሹን በመስመር ሲጨምሩ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች ከነተሸከርካሪው በጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑም በዚህ መሰል ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችም ሆኑ ፋብሪካዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ፤ ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፈው የተገኑ አካላትን በህግ እንደሚጠይቅ ያስገነዝባል፡፡