ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አስጀምሮ ላስጨረሰን ፈጣሪ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል፡፡ዛሬ የተቀዳጀነው ድል ትርጉሙ ብዙ ነው ያሉት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በአንድ በኩል በመጠጥ ውሃ ችግር ሲሰቃይ የነበረውን የአዲስ አበባ ነዋሪ ችግር የሚያቃልል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ፕሮጀክቱ የሚለማበት አካባቢ ነዋሪዎችን የጋራ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑ እንዲሁም ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ጥራትና ሁኔታ መጠናቀቁ ድሉን ድርብ ድርብርብ ያደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡የአዲስ አበባና አጎራባች ህዝቦች አንዱ ያለ ሌላው መኖር የማይችሉ ናቸው ያሉት ከንቲባዋ አዲስ አበባ ከ85 በመቶ በላይ የውሀ አቅርቦቷን የምታገኘው በዙርያዋ ከሚገኙ የኦሮምያ ልዮ ዞን እንደመሆኑ የልማት ስራዎችንም ስናስብ አብሮ መልማትንንና የጋራ ተጠቃሚነትን በአብሮነትና በመከባበር የጋራ እሴቱንም በመገንባት ላይ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ ይህንን ሊነጣጠል የማይችል ግንኙነት የማያውቁና የማይገባቸው አንዳንድ የግል ፍላጎታቸውንና ማካሄድ የሚፈልጉ አካላት ህዝቡን የሚያስከፋ አስተሳሰብ ሲያንፀባርቁ ስለምንመለከት እባካችሁ ከዚህ ድርጊታችሁ ተቆጠቡ ልንል እንወዳለን ብለዋል፡፡ፕሮጀክቱ የታቀደው ለሶስት አመት ቢሆንም በሁለት አመት ውስጥ ተገንብቶ ማጠናቀቅ መቻሉ ለይስሙላ ሳይሆን ጀምረን የመጨረስ የጠቅላይ ሚኒስትራችን ሞቶ በተግባር የዋለበትም ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ፈተና አያስቆመንም ፤ይልቁንም ብርቱ ማስፈንጠርያ አድርገን እንጠቀምበታለን ብለዋል ከንቲባዋ ሰላማችንን እንንከባከብ ፤ለሰላም ሁላችንም አስተዋፅኦ እናድርግ ያሉም ሲሆን ለዚህ ፕሮጀክት አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በበኩላቸው የከተማዋ እድገት የውሃ ፍላጎቱን በእጅጉ እንደጨመረው ገልፀው የከተማ አስተዳደሩ ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮችን ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ዛሬ የተመረቀው ፕሮጀክት ትልቁ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት መሆኑን የገለፁት ኢንጂነር ዘሪሁን የከተማዋን የውሀ ችግር ለመፍታት (በተለይም የየካና የጉለሌ) የውሃ ችግር በመፍታት በከፊል የሚያገለግል ፣ መሆኑንም ተናግረዋል።ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት የፊስ ቡክ ገጽ የተወሰደ