ባለስልጣኑ የመዲናዋን የፍሳሽ አወጋገድ ዘመናዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ሲሆን የጉብኝቱ አላማም ፍሳሽ በመስመር ወደ ማጣሪያ ጣቢያ እንዲገባ የተዘረጉ መስመሮችን መሰረት በማድረግ ነዋሪው ከቤቱ ቅጥያ እንዲያሰራ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ፡፡
በባለስልጣኑ ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር ባሉ ሁሉም ወረዳች በተሰራ የመስመር ዝርጋታ እና ቤት ለቤት ቅጥያው ላይም 12 ተቋራጮች እና በ47 ጥቃቅን አነሰተኛ ማህበራት ተሳትፈዋል ፡፡
ጉብኝቱም በተለይ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረ የወረዳ 10 በተለምዶ ቀይ አፈር ተብሎ የሚጠራ አካባቢን ጨምሮ የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ እና ሌሎች አካባቢዎችን ያካተተ ነው፡፡