የለገዳዲ ክፍል ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ በዚህ በጀት ዓመት መጨረሻ ይጠናቀቃል፡፡የውሃ ፕሮጀክቱ በ4.2 ቢሊዮን ብር የመንግስት በጀት እየተሰራ ያለ ሲሆን ከ860ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ፡፡ፕሮጀክቱ በቀን 86ሺኅ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችል ነው፡፡የውሃ ፕሮጀክቱ 16 ጥልቅ ጉድጓዶች፣ እያንዳንዳቸው ከ2000 እስከ 5000 ሜትር ኪዩብ ውሃ መያዝ አቅም ያላቸው 10 የውሃ ማጠራቀሚያ ጋን ግንባታን፣የ12 ኪሎ ሜትር ዋና የውሃ መሰመር ፣72 ኪሎ ሜትር የውሃ ማሰባሰቢያ መስመር ፣99 ኪሎ ሜትር የስርጭት መስመር ዝርጋታ ፣ሁለት ግዙፍ የግፊት መስጫ ጣቢያዎች እና 38 ኪሎ ሜትር የመዳረሻ መንገድን ያካትታል፡፡ከዚህም በተጨማሪ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች እና በጉድጓዶቹ አከባቢ የሚሰሩ የሲቪል ስራዎች የፕሮጀክቱ አካል ናቸው፡፡ የቻይናው ሲጂሲ ኦሲ (CGCOC) እና በሀገር በቀሉ አሰር ኮንስትራክሽን እየተሰራ ያለው ይህ ፕሮጀክት በጥሩ የግንባታ አፈጻጸም ላይ ይገኛል፡፡