የኘሮጀክቱ ሥም፡      የለገዳዲ ግድብ  ጥገና/ማሻሻያ ጥናት እና ግንባታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በኦሮሚያ ከተማ ለገዳዲ

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ስርጭት የሚካሄድባቸውን የገጸ ምድር ውኃ ማጣሪያ ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነውን የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ የውሃ ግፊት መስጫ ፓምፖች እና ተያያዥ መሳሪያዎች በአገልግሎት ዘመን ብዛት ሙሉ ለሙሉ ከስራ ውጪ ከመሆናቸው በፊት በማደስ የውሃ ስርጭት ሲስተሙን አሰተማማኝ ማድረግ ነው፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- በረዥም ዘመን አገልግሎት ምክንያት በሚጠበቀው ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ የማይገኙት የውሃ ግፊት መስጫ መሳሪያዎችን በማደስ የብክነት እና ወጪ ቆጣቢ የግፊት መስጫ ጣቢያ እንዲኖር በማስቻል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • በአገልግት ዘመን ተደጋጋሚ ብልሽት የገጠማቸውና እና መለዋወጫ የሌላቸውን ጣቢዎች የመለየት ጥናት ማካሄድ
  • የግንባታ ስራ ማከናወን

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ2008 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ2009 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 89,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከገፀ ምድርና ከርሰ ምድረ የሚያመርተውን የመጠጥ ውሃ የከተማው አቀማመጥ ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ ከተገነቡ  የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖች በግራቪቲ እና በግፊት መስጫ ፓምፖች በመጠቀም ለከተማው ነዋሪዎች እና በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ተቋማት ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያሰራጫል፡፡

ቀዳሚ ከሆኑት የገፀ ምድር ውሃ መገኛ ገፈርሳ እና ለገዳዲ ግድቦ የተመረተውን ውኃ ለማሰራጨት ከ40 ዓት በፊ የተገነቡ የግፊት መስ ፓምፕ ጣያዎች በእድሜ ብዛት ያመረቷቸው ኩባኒያዎች መለዋወጫ እያመረቱላቸው ባለመሆኑ ለጥገና መለዋወጫ ከገበያ ላይ ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ ከውሃ ማራቀሚያ ጋኖች ወደ ፓምፖች እንዲሁም ከፓምፖች ወደ ማስረጫ መረቡ የሚያገናኙ ከብረት የተሰሩ ቧንቧዎች መገጣጠሚያዎች ከእድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት በተደጋጋ ጥገና የተካሄደላቸው ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የሚገኘቡ ደረጃ ሙሉ ለሙሉ መታደስ የሚስፈልገው ሆኗል፡፡

የግፊት መስጫ ጣቢያዎቹ አሁን የሚገኙበት ደረጃ በማጥናት የማደስ ስራ በመስራት የግፊት መስጫ ፓምፖች እና ተያያዥ መሳሪያዎችን ዘመናዊ ከማድረጉም በላይ የፓምፖቹን ኢፊሸንሲ እና በግፊት መስጫ ጣቢዎች የሚባክነውም የተጣራ ውሃ መጠን የሚቀንስ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ይህ የግፊት መስጫ ጣቢዎችነ የማሻሻል ፕሮጀክት የግፊት መስጫ ጣቢዎቹን የኤሌክትሪክ ኃልል አጠቃቀም የሚያሻሽል ይሆናል፡፡

ከላይ በዝርዝር በተቀመጡት ምክንያቶች እና ፕሮጀክቱ እንደሚያስገኝ የሚጠበቁ ጥቅሞችን በማገናዘብ በ2007 በጀት ዓመት ይህ ፕሮጀክት ተቀርጿል

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

በአፍሪካ መድረክ ከፍተኛ የፖለቲካ ሚና ያላት አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፍላጎትን ለማሟላት በርካታ የውሃ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ እነዚህ የውኃ ምርት ስራዎች ተሰርተው ወደ ህብረተሰቡ ለማሰራጨት ነባርና አዳዲስ የግፊት መስጫ ጣያዎች ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ከውኃ ብክነት የፀዱ እና ወጪ ቆጣቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ወጪ ቆጣቢ የስርጭት ሲስተም ተግባራዊ በማድረግ ለህበረተሰቡ የሚሰራጨውን የመጠጥ ውሃ አስተማማኝ ለማድረግ ለረዥም ጊዜ በማገልገላቸው ያረጁ፣ ከምርት የወጡ እና ኢፊሸንሲያቸው የቀነሱ ፓምፖችን፣ ቧንቧዎችን፣ ፊቲንጎችን እና ወ.ዘ.ቱ በጥናት በመለየት በዘመኑ ቴክኖሎጂ መቀየርና ውጤታማነታቸውን ማሳደግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ40 ዓመት በላይ ሲጠቀምባቸው የቆዩትን መሳሪያዎች ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ ከመሆናቸው በፊት በጥናት እየለየ በየዓመቱ በጀት በመጠየቅ የማደስ ስራ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

የአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ስርጭት የሚካሄድባቸውን የገጸ ምድር ውኃ ማጣሪያ ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነውን የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ የውሃ ግፊት መስጫ ፓምፖች እና ተያያዥ መሳሪያዎች በአገልግሎት ዘመን ብዛት ሙሉ ለሙሉ ከስራ ውጪ ከመሆናቸው በፊት በማደስ የውሃ ስርጭት ሲስተሙን አሰተማማኝ ማድረግ ነው፡፡

የሥራው ግብ

በረዥም ዘመን አገልግሎት ምክንያት በሚጠበቀው ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ የማይገኙት የውሃ ግፊት መስጫ መሳሪያዎችን በማደስ የብክነት እና ወጪ ቆጣቢ የግፊት መስጫ ጣቢያ እንዲኖር በማስቻል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • የታደሰ፣ እድሜው የተራዘመ፣ ለተደጋጋሚ ብልሽት ያልተጋለጠ፣ ወጪ ቆጣቢ የግፊት መስጫ ጣቢያዎች በመተከላቸው ህብረተሰቡ ያልተቆራረጠ የውሃ ስርጭት እንዲያገኝ ያስችላል፡፡

በ2008 የሚከናወኑ ተግባራት

  • ለውሃ ማምረቻ ጣቢያዎቹ የኤሌክትሪክ ሃይልን የሚተካ አማራጭ ሃይል ጥናት ሥራ ማጠናቀቅ፣
  • የኤሌክትሪክ ሃይልን ለሚተካ አማራጭ ሃይል ትግበራ ሥራ የተቋራጭ/የዕቃ አቅራቢ ቅጥር መፈጸም፣
  • የሱፐርቪዥን ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የዝርዝር ጥናት ዲዛይን ሥራ የሚያከናውን አማካሪ መቅጠርና የጥናት ሥራውን መከታተል፤

ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • ዝርዝር ጥናቱን የሚያጠና አማካሪ የሚቀጠር ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን በሙሉ አማካሪ ድርጅቱ ያቀርባል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርአት

  • የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ለመከታተል ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርቶችን መከታተል፡፡
  • የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ በመገምገም እቅዱን መከለስ

በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/

ይህንን ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡

 

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
32 የለገዳዲ ግድብ ጥገና/ማሻሻያ ጥናት እና ግንባታ ፕሮጀክት   21,578,750 21,578,750 0 0 0
32.1 የለገዳዲ ግድብ ጥገና/ማሻሻያ ጥናት ሥራ ማከናወን 6,979,954 1,178,750 1,178,750 በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለጥናት ሥራው የሚከፈል በጀት ነው፡፡ ጥናቱ የ4 ወር ጥናት ነው፡፡
32.2 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የለገዳዲ ግድብ ጥገና/ማሻሻያ ትግበራ ሥራ ማከናወን 80,000,000 20,000,000 20,000,000 ከትግበራ ሥራው ጋር በተያያዘ ኤልሲ ለማስከፍት እና ለቅድመ ክፍያ የሚውል በጀት ነው፡፡ ሥራው የ12 ወር እንደሚሆን ይገመታል፡፡
32.3 የሱፐርቪዥን ሥራ ማከናወን 1,200,000 400,000 400,000 በሚገባው ውለታ መሠረት በወር 100ሺህ ብር ለመክፍል በ2008 በጀት ዓመት ለ4 ወር የሚከፍል በጀት ነው፡፡