የኘሮጀክቱ ሥም”:- የምስራቅ ተፋሰስ የፍሳሽ ግንባታ ፕሮጀክት  

የአስፈጻሚው አካል በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ፕሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ የአዲስ አበባ ከተማ ምስራቅ አዲስ አባ ክፍል

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ አላማ 

የምስራቅ አዲስ አበባ አካባቢን የፍሣሽ አገልግሎት እንዲዳረስ ማድረግ

የፕሮጀክቱ ግብ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኮምፖነንት 2 ስራ በማከናወን ወደ 500000 የሚጠጋ የምስራቅ አዲስ አበባ ህብረተሰብ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች

  • የኤሌክትሮ ሜካኒካል መሳሪያዎች ግዥና ተከላ ማከናወን፣
  • የህንጻ ግንባታ ሥራዎች
  • የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ማከናወን
  • የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ማከናወን፣
  • የመዳረሻ መንገድ ግንባታ ማከናወን፣
  • ከፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን የካሳ ክፍያ መፈጸም፣

የሚጠበቅ ውጤት

  • በአጠቃላይ ወደ ግማሽ ሚሊዮን ለሚጠጋ ሕዝብ የፍሣሽ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ

ፕሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ

  • 2ዐዐ2 ዓ.ም 

ፕሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ

  • 2012 ዓ.ም የመጀመሪያው ክፍል

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት ግምት

  • 3,361,412,000

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን እ.አ.አ በ2ዐዐ2 የአዲስ አበባን የፍሣሽ ማስተር ኘላን ክለሣን አስጠንቷል፡፡ ከዚህም በመቀጠል በ2ዐዐ4 ዓ.ም DHL ከተባለ አማካሪ አማካይነት የምሥራቅ አዲስ አበባን የውሃና ፍሣሽ ማስወገጃ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለማስፋፋት ጥናት ተደርጓል፡፡

የዚህ ኘሮጀክት ለግንባታ የሚሆን የመጨረሻ ዲዛይን ሥራ በ 2002 በጀት ዓመት መግቢያ ተጠናቋል፡፡ በጥናቱ በተቀመጠው መሠረት በ 2003 በጀት ዓመት የመሣሪያዎች ግዥና ተከላ፣ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ እና የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራዎች በከፊል የሚጀመሩ ይሆናል፡፡

ፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

የምስራቅ አዲስ አበባ አካባቢ በፈጣን እድገት በመልማት ላይ ያለ ቢሆንም አካባቢው ምንም ዓይነት የፍሣሽ መስመር እና የፍሣሽ ማጣሪያ ተገንብቶለት አያውቅም፡፡

በምስራቅ አዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት ከ15ዐ ሺህ በላይ አባዎራዎችን የሚይዙ ኮንዶሚኒየም ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንዱስትሪወች፣ ሪል ስቴቶች እና ሌሎችም የልማት ሥራዎች በማፋጠን ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህም መሠረት ከፍተኛ የሆነ የፍሣሽ ማስወገጃ ፍላጐቶች ከሕብረተሰቡ ቀርቧል፡፡ የዚህ ኘሮጀክት ተግባራዊ መሆንም እ.ኤ.አ እስከ 2ዐ25 ያለውን የፍሣሽ ማስወገጅ ፍላጐት ምላሽ ይሰጣል፡፡

ፕሮጀክቱ ዓላማ

የምስራቅ አዲስ አበባ አካባቢ ፍሣሽ በአካባቢና ጤና ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የፍሣሽ ማሰብሰቢያ መስመሮችንና የፍሣሽ ማጣሪያ ኘላንት እንዲገነባ ማድረግ፣

ፕሮጀክቱ ግብ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኮምፖነንት 2 ስራ በማከናወን ወደ 500000 የሚጠጋ የምስራቅ አዲስ አበባ ህብረተሰብ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ሥራውን ተግባራዊ በማድረግ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የፍሣሽ ማስወገጃ ሥርዓት እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል፡፡ በዚህም

  • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል
  • የአካባቢ ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፣
  • የአካባቢ ብክለትን ማስወገድና የተሟላ ጤና እንዲኖር ያደርጋል፣
  • የፀዳች አዲስ አበባና ለቱሪስት የምትመች ከተማ እንዲኖረን ያደርጋል፣
  • ተጨማሪ ሥራ በመስራት የተጣራውን ፍሣሽ ለመስኖ እንዲውል በማድረግ የአካባቢ ግብርና እንዲስፋፋ ለማድረግ ይቻላል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም የምስራቅ ተፋሰስ ማጣሪያ ጣቢያ እና የመስመር ጥናት እና ዲዛይን ስራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የዕቃ ግዥ ጨረታ በማውጣት፣ የፍሳሽ መሳሪያዎች( Electro mechanical equipment) ከነመገጣጠሚያቸው እንዲገዙ ማድግ፣
  • ከዕቃ ግዥው ሥራ ጐን ለጐን ጨረታ ማውጣት ግንባታ የሚገነባ ተቋራጭ መምረጥ እና ግንባታ ማስጀመር፣

ፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • ኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎችና መሳሪያዎች፣
  • የግንባታ ግብአቶች

የአካባቢና ነባራዊ ሁኔታዎች 

በጥናቱ መሠረት አሉታዊ ተጽኖዎች ለማስቀረትና በጐ ተጽኖዎችን ለማሣደግ የሚችል ሥራ ይሰራል፡ ዋና ዋናዎቹም፡-

  • በግንባታ ወቅት የሚያጋጥሙ የወሰን ማስከበር ሥራዎችን በቅድሚያ መፍታት
  • ለሚነሱ መሰረተ ልማቶችና ቤቶች ካሣ መክፈል እና የመሣሠሉት ናቸው፡፡

የክትትል እና ግምገማ ሥርዓት

የግንባታ ሥራ በሚጀመርበት ወቅት አማካሪው በሚያቀርበው የሥራ ክትትል ሥልት መሠረት እና ባለቤቱ በሚመድባቸው መሀንዲሶች እና ሌሎች ባለሙያዎች መሠረት የሥራ ሂደት ክትትል ይደረጋል፡፡ የክትትል መመዘኛ ነጥቦችም በጨረታ እና ስምምነት ሰነዶች ላይ እንዲኖሩ ይደረጋል፡፡

ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች

የሚከተሉት ነጥቦች ፕሮጀክቱን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የሚያጋጥሙ ስጋቶችና ምቹ ሁኔዎች ናቸው፡፡

ሀ/ ስጋቶች

  • በጀቱን ከቱርክ መንግስት በወቅቱ ያለማግኘት፣
  • የወሰን ማስከበር ችግር፣
  • የባለ ድርሻ አካላት ድርሻቸውን ያለመወጣት ችግር፣

ለ/ ምቹ ሁኔታዎች

  • ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ የመንግሥት ቁርጠኝነት፣
  • በአካባቢው ያለው የኢንቨስትመንት እና ልማት መስፋፋት፣
  • በአካባቢው የተገነቡ እና በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶች እና ሌሎች ተቋማት፤ ዘመናዊ የፍሣሽ መሠብሰቢያ እና ማጣሪያ ኘላንት የሚፈልጉ መሆናቸው፣
  • ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች፣

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት ግምት 

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
13 የምስራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ እና ፈሳሽ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት   29,479,998 0 29,479,998 0 0
13.1 ዝርዝር የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን 110,000,000 16,500,000 16,500,000 ጥናቱ የ1 ዓመት ሲሆን በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለኢንሰምሽን ሪፖርት የሚከፈል በጀት ነው፡፡
13.2 የካሳ ክፍያ መፈጸም 12,979,998 12,979,998 12,979,998 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡