የኘሮጀክቱ ሥም፡    የሲስተም ማኔጅመንት ጥናት ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያሉትን የውሃ አውታሮች በተቀናጀና ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ ለትውልድ በሚተላለፍ መልኩ እንዲቀመጡ ማድረግና የሚገነቡት አዳዲስ ግንባታዎች ቀድሞ በተዘረጋው መስመር ላይ የሚኖራቸውን አሉታዊ አውንታዊ ተጽዕኖ በአግባቡ ያገናዘበ የዲዛይን ሥራ መስራት፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- የሲስተም ማኔጅመንት ጥናት በማካሄድ የውኃ ሥርጭት ስርዓቱን በመቆጣጠር የተጠናከረ የመረጃ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የGIS፣ ሀይድሮሊንክ ሞዴሊንግ እና NRW ጥናት ማከናወን
  • የትግበራ ሥራ ማከናወን
  • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም የዲስትሪቢውሽን ኔትወርክ ሞዴሊንግ ሥራ ማከናወን
  • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም የcall center system ጥናትና ትግበራ ሥራ ማከናወን

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2002 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2007 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 103,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

የአዲስ አበባ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋችና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገቶችን እያሳየች እንደመምጣቷ መጠን የሚኖረውን የውሃ ፍላጉት ጥያቄ በአፋጣኝ ለመመለስ በሚሰሩ አጣዳፊ ስራዎች ምክንያት የተሟላ መረጃ ሳይያዝላቸው ወደስራ የገቡና በመሬት ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ብዙ የውሃ መስመሮች አሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከተዘረጉ ረጅም እድሜ ያስቆጠሩና መኖራቸውም በአግባቡ የማይታወቁ መስመሮች በስፋት ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ስለመስመሮቹ ያለው የመረጃ አያያዝና ፍሰት የተደራጀና ዘመናዊ ባለመሆኑ ምክንያት በስራው ላይ ከፍተኛ እንቅፋትን የፈጠረ ከመሆኑም አልፎ አስፈላጊው የኢንጂነሪንግ ማረጋገጫ ሣይሰጥባቸው የሚዘረጉ መስመሮችን ብዛት ከፍ አድርጐታል፡፡

በመሆኑም የዚህ ሥራ ተግባራዊ መሆን የመረጃ አያያዙን ፍሰት የተቀላጠፈና ዘመናዊ የሚያደርገው ሲሆን፤ አዲስ የሚዘረጉ መስመሮች ከቀድሞው መስመር ጋር የሚኖራቸው ቅንጅትና የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ በምህንድስና ገምግሞ ወደ ስራው መግባት የሚቻልበትን የሃድሮሊክ ሞዴሊንግ ሥራ ስርዓትን ለመዘርጋት ያስችላል፡፡

የሥራው አስፈላጊነት

የባለስልጣን መ/ቤቱ የመረጃ አያያዝና ፍሰት የተቀናጀና ዘመናዊ እንዲሆን ከማድረግ አንጻር እንዲሁም ከአጠቃላይ የከተማው ማስተር ኘላን አንጻር ከሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮች አንጻር እንዲሁም የተቀናጀ የከተማ ጂ.አይ.ኤስ መረጃ መቅረፅ አንጻር ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚኖረው ሲሆን የውሃ ስርጭት ስርዓቱ በተቀላጠፈ ሁኔታ መቆጣጠር ያስችላል፡፡

የሥራው ዓላማ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያሉትን የውሃ አውታሮች በተቀናጀና ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ ለትውልድ በሚተላለፍ መልኩ እንዲቀመጡ ማድረግና የሚገነቡት አዳዲስ ግንባታዎች ቀድሞ በተዘረጋው መስመር ላይ የሚኖራቸውን አሉታዊ አውንታዊ ተጽዕኖ በአግባቡ ያገናዘበ የዲዛይን ሥራ መስራት፡፡

የሥራው ግብ

የሲስተም ማኔጅመንት ጥናት በማካሄድ የውኃ ሥርጭት ስርዓቱን በመቆጣጠር የተጠናከረ የመረጃ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ሥራው ሲጠናቀቅ የተቀላጠፈና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝና ፍሰትን ይፈጥራል፡፡ እንዲሁም አዳዲሶቹ ግንባታዎች በነባሮቹ ላይ የሚኖራቸውን አሉታዊ ተጽዕኖ ይቀርፋል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም የዲስትሪቢውሽን ኔትወርክ ሞዴሊንግ ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የከተማዋ ክፍል ውስጥ የጂ.አይ.ኤስ ሥራ መስራት

ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

  • ጥናቱን የሚያጠናና ከተመረጠው የከተማዋ ንዑስ ክፍል ውስጥ የጂ.አይ.ኤስ ስርዓት የሚዘረጋ አማካሪ የሚመረጥ ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን አሟልቶ ሥራውን ይሰራል፡፡ በሥራው ላይ በቀጣይ እንዲሳተፉ ለተመረጡ የድርጅቱ ሠራተኞች ስልጠና ይሰጣል፡፡

የአካባቢና የማሕበራዊ ትንታኔ

ይህ ሥራ የሚስከትለው አካባቢያዊም ሆነ ማህበራዊ ተፅዕኖ የለውም፡፡

በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰት ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
36 የሲስተም ማኔጅመንት ጥናት ፕሮጀክት   12,000,000 12,000,000 0 0 0
36.1 የዲስትሪቢውሽን ኔትወርክ ሞዴሊንግ ጥናት ሥራ ማከናወን 60,000,000 12,000,000 12,000,000 ጥናቱ የ2 ዓመት ከ6 ወር ሲሆን በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለጥናት ሥራው የሚከፈል በጀት ነው፡፡