የኘሮጀክቱ ሥም፡    የተቋማት ግንባታ ቁ.2 ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ በመገናኛ እና በለገዳዲ አካባቢ

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡-

  • የመገናኛ ቅ/ጽ/ቤት ግንባታ በማከናወን በቅርበት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት
  • በለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ የኦፕሬተሮች ማረፊያ ቤት በመገንባት የማጣሪያ ጣቢያውን ሥራ ማጠናከር፡፡

ግብ ፡-የተለያዩ የተቋማት ግንባታ በማከናወን የመ/ቤቱን ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የቅ/ጽ/ቤቶች እና የኦፕሬተሮች ማረፊያ የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን፣
  • የመገናኛ ቅ/ጽ/ቤቶች ግንባታ
  • የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ የቢሮ ኦፕሬተሮች ማረፊያ ግንባታ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2004 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2007 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 118,061,786 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

 

መግቢያ

ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጥሩ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በአገልግሎት ቦታ ችግር እና በማጣሪያ ጣቢያዎች የኬሚካል ግምጃ ቤት አለመሟላት ምክንያት የታሰበውን ውጤት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በ2005-07 በጀት ዓመት የተለያዩ የአገልግሎት መስጫዎችን በመገንባት ችግሩን ለመፍታት ታቅዷል፡፡ በዚህም መሠረት የቢሮ ግንባታ እና የኦፕሬቶች ማረፊያ ግንባታ ዋና ዋና ተግባራት ሆነው ተመርጠዋል፡፡ የፕሮጀክቱ መተግበር የአገልግሎት ተጠቃሚው ህብረተሰብ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ እና የባለሥልጣን መ/ቤቱን የቴክኒክ የማሰፈፀም አቅምን ከፍ ያደርገዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

የተቋማት ግንባታ ፕሮጀክት የቅ/ጽ/ቤቶች እና የፕ/ጽ/ቤትን አገልግሎትን በማቀላጠፍ የባለሥልጣን መ/ቤቱን የቴክኒክ ክፍል በማሳደግ በማጣሪያ ጣቢያ ውስጥ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት በኩል በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

  • የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በመገንባት ጥራቱን የጠበቀ የአገልግሎት መስጫ በማስገንባት ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት
  • የባለሥልጣን መ/ቤቱን የቴክኒክ አቅም መገንባት፣
  • በውሃ ማጣሪያ ጣቢያዎች አካባቢ የሚታየውን የመሠረት ግንባታዎች በማስፈፀም የጣቢያውን እንቅስቃሴ ማጠናከር፣

የፕሮጀክቱ ግብ የተለያዩ የተቋማት ግንባታ በማከናወን የመ/ቤቱን ተቋማዊ አቅም እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

የሚጠበቁ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  1. ለቅ/ጽ/ቤቶች እና ለፕሮጀክት ጽ/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት
    • የአካባቢው ሕብረተሰብ በቅርበት የተሟላ አገልግሎት ያገኛል፣
    • የባለሥልጣን መ/ቤቱ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት የማስፈፀም አቅሙን ይበልጥ ያሳድጋል፣
    • በየጊዜው ለቢሮ ኪራይ የሚወጣውን ገንዘብ በማስቀረት የመንግሥትን በጀት በአግባቡ ለመጠቀም ያስችለዋል፡፡
  2. ለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ ያሉትን ግንባታዎች ማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት፡፡ በዚህም ተጠቃሚ ሕዝብ ጥራቱን የጠበቀ ውሃ እንዲያገኝ ያስችላል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • ቀሪ የመገናኛ ቅ/ጽ/ቤት ግንባታ ስራ ማከናወን
  • የለገዳዲ የእንግዳ ማረፊያ እና ኦፕሬተሮች ቤት ግንባታ ስራ ቀሪ የመያዥያ ክፍያ
  • የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ

የአፈፃፀም ስልቶች

  • ቀጥተኛ የፕሮጀክት ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሥራዎች የዕለት ተዕለት ቁጥጥር ማካሄድ፣

ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብአቶች

  • ሲሚንቶና የሲሚንቶ ውጤቶች፣ የግንባታ ብረቶች፣ ማናቸውም ተጓዳኝ የግንባታ ግብአቶች፣
  • የስለጠነ ባለሙያ፣

የአካባቢና ማህበራዊ ትንታኔ

የግንባታ ሥራዎች በሚገኙበት አካባቢ ለሚኖሩ አነስተኛና ጥቃቅን ድርጅቶች ለቀን ባለሙያዎችና ለአገር ውስጥ ከፍተኛና መለስተኛ ተቋራጮች ጥሩ የሥራ ዕድል ስለሚከፍት ጥሩ የማህበራዊ እሴት ይኖራቸዋል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርዓት 

  • የፕሮጀክቶችን እንቅስቃስ ለመከታተል ሳምንታዊና ወራዊ የሳይት ሪፖርቶችን መከታተል፣
  • ወርሃዋ የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት ዕቅዱንና አፈፃፀሙን በየወሩ በመገምገም፣
  • የፕሮጀክቶዡን እንቅስቃሴ ዕቅድንና አፈፃፀሙን በማቀናጀት ለሚመለከተው አካል መላክ፣
  • የፕሮጀክቶች ዕቅድ ከፊዚካል አፈፃም ጋር አለመጣጣም ሲገኝ እቅዱን መከለስ፡፡

ሥጋትና ምቹ ሁኔታዎች

የተቋማትን ግንባታ ፕሮጀክቶችን በታሰበላቸው ግብ ለመሰራት የሚያጋጥሙ ዋና ሥጋቶች፣

  • የግንባታ ግብአቶች በበቂ ሁኔታና በታሰበ ጊዜ አለመገኘት፣
  • የግንባታ ግብአቶች ዋጋ መጨመር፣
  • በቂ የሰለጠነ ባለሙያ አለማግኘት፣

ምቹ ሁኔታ

  • መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት
  • ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በባለሙያዎች ለፕሮጀክቶቹ ተግባራዊነት በሙሉ አቅማቸው መትጋት፣

የ2007 በጀት ዓመት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ በጀት 20,926,025 ሲሆን ዝርዝር በጀቱ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
23 የተቋማት ግንባታና የተጠናቀቁ ጥናቶች መተግበር ቁ.2 ፕሮጀክት   20,926,025 20,926,025 0 0 0
23.1 የመገናኛ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ግንባታ ስራን ማጠናቀቅ፡፡ 50,111,794 20,022,359 20,022,359 ይህ ፕሮጀክት ስራው በ2008 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን የ2.5 መያዣ ክፍያን ጨምሮ 20 ሚሊዮን ብር በሚቀጥለው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ውስጥ እንሚከፈል ታሳቢ ተደርጎ በጀቱ ተይዟል፡
23.2 የለገዳዲ የኦፐሬተሮች እና የእንግዳ ማረፊያ ግንባታ 17,039,403 753,666 753,666 የዚህ ግንባታ ስራ በ2007 በጀት አመት የተጠናቀቀ በመሆኑ ለቀጣዩ የበጀት አመት የ2.5 በመቶ የስራ ዋስትና የተያዘ በጀት ነው፡፡
23.3 የሱፐርቪዥን ክፍያ መፈጸም 150,000 150,000 150,000 በተገባው ውለታ መሠረት ለግንባታ ቁጥጥር ሥራው ለ2 ወር የሚከፍል በጀት ነው፡፡