የኘሮጀክቱ ሥም፡    የንጹህ መጠጥ ውሃ ስርጭት እና የፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-በአዲስ አበባ ከተማ

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) ማወቅ እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሰነድ ማዘጋጀት ነው

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-አሁን ያለውን የከተማዋን የመጠጥ ውኃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) በማወቅ እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሰነድ በማዘጋጀት በቀጣይ በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል ያለውን ልዩነት ስትራቴጂክ በሆነ መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • በከተማዋ ውስጥ ያለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ስርጭት (water coverage) ሽፋን መጠን እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ ልማት Road Map ጥናት ሥራ ማከናወን
  • በከተማዋ ውስጥ ያለውን የፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት (sewer coverage) ሽፋን መጠን እንዲሁም የረዥም ጊዜ የፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሥራ ማከናወ

ከኘሮጀክቱ የሚጠበቅ ውጤት

ይህ ኘሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን

  • የከተማዋ የወቅቱ የመጠጥ ውኃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) በጥናት በተደገፈ መልኩ ይታወቃል፣
  • የከተማዋ የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሰነድ በአማሪ ተሰርቶ ለትግበራ ዝግጁ ይሆናል

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ2007 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ2008 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት

  • ከ10,000,000 ብር በላይ ይፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን በመጠጥ ውሃ ችግር ውስጥ እየተዘፈቀ የሄደውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ችግር ለመቅረፍ መንግሥት የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ኘሮጀክቶችን ለመተግበር በርካታ የጥናት ሂደቶችን አጠናቋል፡፡ የጥናት ሂደቶቹ የከርሰምድርና የገፀ ምድር የውሃ ሀብቶችን ማዕከል ያደረጉ ሲሆን በተለይ የከርሰ ምድር የውሃ መገኛ ጥናት የከተማውን የውሃ ፍላጐት በአጭር ጊዜ ከመፍታት አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

ኘሮጀክት ጽ/ቤቱ የሚያስቆፍረው ይህ ሥራ የጽ/ቤቱን የማስፈፀም አቅም በሰው ኃይል በማሳደግ እንዲጠናከር ያደርጋል፡፡ ይህ ተግባር በውስጥ የዘርፍ ተቋማት፣ የሚከሰተውን ችግር በመቅረፍ እና አነስተኛ /መለስተኛ/ ጥልቅ ጉድጓዶች የሚገኘውን አነስተኛ ምርትና በየጊዜው የሚከሰተውን የውሃ ምርት መጠን በማስወገድ ከፍተኛ ውጤት ይሰጣል፡፡

የኘሮጀክቱ አስፈላጊነት

በአፍሪካ መድረክ ከፍተኛ የፖለቲካ ሚና ያላት አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን የንፁህ መጠጥ ውሃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ጥያቄን ለመመለስ ሳትችል ለበርካታ ጊዜ ቆይታለች፡፡ በቅርብ የተደረጉ አንዳንዱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከተወሰኑት የከተማው አካባቢዎች በስተቀር በአዲስ አበባ የ24 ሰዓት የውሃ ሽፋን የሚያገኙ አካባቢ እጅግ ውስን ከመሆናቸውም በላይ ችግሩ ይበልጥ በተጠናከረባቸው በፈረንሣይና በአስኮ አካባቢዎች በ15 ቀን ፈረቃ የቧንቧ ውሃ የሚሰራጭበት አካባቢ እንዳለ ይታወቃል፡፡በፍሳሹም ረገድ አብዛኛው የከተማዋ ህብረተሰብ ክፍል የዘመናዊ ፍሳሽ መስመር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ታውቋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን በመንደፍ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እነዚህ በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ ተቀርጸው ሲከናወኑ የነበሩ የውኃና ፍሳሽ የልማት ስራዎች በተጨባጭ በህብረተቡ ዘንድ ያስገኙትን ውጤት ለማወቅ አጠቃላይ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የመጠጥ ውሃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) ማወቅ ለቀጣይ ሥራዎች የሚኖረው አስተዋጾ የጎላ ይሆናል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በቀጣ አመታት በከተማዋ ውስጥ የሚኖረውን የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዕድገት ከግንዛቤ በማስገባት የተቀናጀ የፍሳሽ እና የውኃ የረዥም ጊዜ የልማት Road Map ጥናት ሰነድ ማዘጋጀት የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ይሆናል፡፡ በመሆኑም እነዚህን 2 የተለያዩ ሥራዎች ለማሰራት ይህ ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡

የኘሮጀክቱ ዓላማ

የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) ማወቅ እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሰነድ ማዘጋጀት ነው

የኘሮጀክቱ ግብ

አሁን ያለውን የከተማዋን የመጠጥ ውኃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) በማወቅ እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሰነድ በማዘጋጀት በቀጣይ በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል ያለውን ልዩነት ስትራቴጂክ በሆነ መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ይህ ኘሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን

  • የከተማዋ የወቅቱ የመጠጥ ውኃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) በጥናት በተደገፈ መልኩ ይታወቃል እንዲሁም
  • የከተማዋ የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሰነድ በአማሪ ተሰርቶ ለትግበራ ዝግጁ ይሆናል

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም የንጹህ መጠጥ ውሃ ስርጭት እና የፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሥራ ማከናወን

የአፈጻጸም ስልቶች

  • የዝርዝር ጥናት ዲዛይን ሥራ የሚያከናውን አማካሪ መቅጠርና የጥናት ሥራውን መከታተል፤

ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግበአቶች

ዝርዝር ጥናቱን የሚያጠና አማካሪ የሚቀጠር ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን በሙሉ አማካሪ ድርጅቱ ያቀርባል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርአት

  • የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ለመከታተል ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርቶችን መከታተል
  • የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ በመገምገም እቅዱን መከለስ

አጠቃላይ እና ዝርዝር በጀት

ይህ ፕሮጀክት ከላይ ለተዘረዘሩት ሥራዎች ማስኬጃ 10,000,000 ብር የሚያስፈልግ ይሆናል፡፡

 

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
35 የንጹህ መጠጥ ውሃ ስርጭት እና የፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ፕሮጀክት   10,000,000 0 10,000,000 0 0
35.1 የንጹህ መጠጥ ውሃ ስርጭት እና የፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት ሽፋን መጠን (water & sewer Coverage) እንዲሁም የረዥም ጊዜ የውኃ እና ፍሳሽ ልማት Road Map ጥናት ሥራ ማከናወን 10,000,000 10,000,000 10,000,000 በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለጥናት ሥራው  የሚከፈል ክፍያ ሲሆን አጠቃላይ ጥናቱ 6 ወር የሚፈጅ ነው፡፡