የኘሮጀክቱ ሥም፡    የአቃቂ ጨፌ ክፍል 2 ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት  

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ቦሌ ቡልቡላ ቦሌ ሚካኤል ወዘተ… ሆኖ ዋና የፍሣሽ መስመሮቹ የሚገነቡ ወይም በመገንባት ላይ ያሉ በአካባቢው የሚገኙ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ያካትታል፡፡

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ቦሌ ቡልቡላ ቦሌ ሚካኤል እና አዲስ የሚገነቡትን የኮንዶሚኒየም ቤቶች እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎችን የፍሣሽ አገልግሎት እንዲዳረስ መድረግ፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-በፍሳሽ ማስተር ፕላኑ መሠረት በአቃቂ አካባቢ የፍሳሽ ማጣሪያ እስከ 2008 በመገንባት በአካባቢው ለሚገኙ የኮንደሚኒየም ቤቶችና ቦሌ ሚካኤል.፣ ቦሌ ቡልቡላ እንዲሁም በርታ ሪል እስቴት አካባቢ ለሚኖሩ ወደ 500,000 ለሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • ለ CHEFE SUB-CATCHMENT እና ለ AKAKI SUB-CATCHMENT የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
  • ለ CHEFE SUB-CATCHMENT እና ለ AKAKI SUB-CATCHMENT የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ሥራ፣
  • የግንባታ ቁጥጥር ሱፐርቪዥን ሥራ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ2007 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ2009 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 250,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን እ.አ.አ በ2ዐዐ2 ዓ.ም የአዲስ አበባን ፍሣሽ ማስተር ኘላን ክለሳ ማስጠናቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ማስተር ኘላን

ኘሮጀክቱ ሁለት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል፡፡ እነዚህም፡

ሀ/ የአቃቂ አካባቢ የፍሣሽ መስመር ግንባታ እና

ለ/ የአቃቂ አካባቢ የፍሣሽ ማጣሪያ ግንባታዎች ናቸው፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

የአቃቂ አካባቢ በከተማችን በከፍተኛ ፍጥነት እድገት በማሣየት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም አካባቢው ምንም አይነት የፍሣሽ ማስወገጃ መስመርና የፍሣሽ ማጣሪያ መስመር አልተገነባለትም፡፡

በአካበቢው በአሁኑ ጊዜ ከ150 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንዱስትሪዎች፣ ሪል ስቴቶች እና ሌሎችም የልማት ተቋማት ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡

ከእነዚህም የልማትና የሰፈራ ኘሮግራሞች ጋር የተያያዘ ከፍተኛ የሆነ የፍሣሽ ማስወገጃ ፍላጐቶች ከሕብረተሰቡ ቀርበዋል፡፡ እንደሚታወቀው የአ.አ.ው.ፍ.ባ አላማም የሕብረተሰቡን የፍሣሽ ማስወገጃ ጥያቄዎች ማስተናገድ እንደመሆኑ ይህንን ኘሮጀክት ቀርጾ አቅርቧል፡፡

የዚህ ሥራ ተግባራዊ መሆንም እ.ኤ.አ እስከ 2ዐ25 የሚኖረውን ፍሣሽ ማስወገድ ፍላጐት ምላሽ ይሰጣል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

የአቃቂ አካባቢ ፍሣሽ በአካባቢና ጤና ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የፍሣሽ መሰብሰቢያ መስመሮችን እና የፍሣሽ ማጣሪያ ኘላንት እንዲገነባ ማድረግ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ

በአቃቂ አካባቢ በሁለት ክፍል (phase) የሚገነባውን በቀን 25 ሺህ ሜ.ኩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ሥራ ክፍል ሁለትን የዲዛይን ክለሳ እና የተቋራጭ ቅጥር ሥራ በማከናወን ግንባታው እንዲጀመር ይደረጋል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ሥራውን ተግባራዊ ለማድረግ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓት እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል፡፡ በዚህም፡

  • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
  • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
  • የአካባቢ ብክለትን ማስወገድና የተሟላ ጤና እንዲኖር ያደርጋል፡፡
  • የፀዳች አዲስ አበባ ብሎም ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ እድገት የተመቸች ከተማ እንድትኖረን ያደርጋል፡፡
  • ተጨማሪ የመስኖ ሥራዎችን ለመስራት የተጣራውን ፍሣሽ ለአካባቢው ግብርና እንዲውል ማድረግ ይቻላል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማጠናቀቅ፣
  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የማጣሪያ ጣቢያውን 21.7 በመቶ ግንባታ ስራ ማከናወን

የክትትልና ግምገማ ሥርዓት

ከአማካሪው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥናቱን በሚገመግሙ ባለሙያዎች እየታዩ መዳበር የሚገባቸው ነጥቦች እንዲዳብሩ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የክትትል መመዘኛ ነጥቦችን በጨረታና በስምምነት ሰነዶች ላይ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡

ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች

ፕሮጀክቱን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃሉ፡

ሀ/ ሥጋቶች

  • የባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን ያለመወጣት ችግር ናቸው፡፡

ለ/ ምቹ ሁኔታዎች

  • ሥራውን ተግባራዊ ለማድርግ የመንግስት ቁርጠኝነት
  • በሕብረተሰቡ በካል ያለው የውሃ ፍላጐት የናረ መሆኑ
  • በአካባቢው ያለው የኢንቨስትመንትና ልማት መስፋፋት
  • በአካባቢው የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት፤ ዘመናዊ የፍሳሽ መሰብሰቢያ እና ማጣሪያ ኘላንት የሚፈልጉ መሆናቸው
  • ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች

ከላይ ለተጠቀሱት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገው ጠቅላላ በጀት 40,596,514 ብር ሲሆን ዝርዝሩም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
15 የአቃቂ ጨፌ ክፍል 2 ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት   40,596,514 40,596,514 0 0 0
15.1 የአማካሪ ቅጥር በመፈፀም የጥናት ክለሳ ሥራ ማከናወን 15,968,679 8,263,179 8,263,179 ለጥናት ሥራው የተያዘ በጀት ነው፡፡ በተገባው ውለታ መሠረት አጠቃላይ ጥናቱ የ3 ወር ነው፡፡
15.2 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ስራ ማከናወን 107,346,681 30,000,000 30,000,000 የግንባታ ሥራው በ2008 በጀት ዓመት 22 በመቶ ይጠናቀቃል በሚል ታሳቢ ለኤሌክትሮሜካኒካል 72.2 ሚሊየን ብር እንዲሁም ለሲቪል ሥራው ቅድመ ክፍያ ብር 7.029 ሚሊየን በድምሩ 79.3 ሚሊየን ብር ለ2008 በጀት ዓመት ተይዟል፡፡ይህ ስራ በአጠቃላይ ሞቢላይዜሽንን ጨምሮ 18 ወራት እንደሚፈጅ ታሳቢ የተደረገ ሲሆን ለዚህም ከዚህ በፊት ከነበሩት 11 ዩኒቶች ውስጥ 4ቱ በዚህ ኮንትራት ተደግመው የማይሰሩ በመሆኑ ነው፡፡ ለአብነትም ኦግዚለሪ ቢውልዲንግ፣ ሳኒተሪ ላንድ ፊል፣ ገሪት ቻምበር እና ሊፍቲንግ ስቴሽን የማይሰሩ ሥራዎች ናቸው፡፡
15.3 የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ 8,400,000 2,333,335 2,333,335 በውል ስምምነቱ መሠረት በየወሩ ለሚያካሄደው የሱፐርቪዥን ሥራ በየወሩ 466,667 ብር የሚከፍል ሲሆን በዚህ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለ5 ወር ክፍያ ለመፈጸም የተያዘ በጀት ነው፡፡