ቋሚ ኮሚቴው በክ/ከተማ ደረጃ ያሉ የቋሚ ኮሚቴ አደረጃጀቶች ከተቋማቱ ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ላይ በማተኮር ነው በኢሊሊ ሆቴል ውይይቱን ያካሄደው ።
በመድረኩ በቅንጅት ከመስራት አንጻር ያለ ችግር ተነስቶ ወይይት ተደርጓል ።
ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ቅርንጫፎቹ ተቀናጅቶ ከመስራት እና አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት አኳያ ያለው አሰራር የሚመሰገን ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ውሃ ፈረቃ መዛባት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ባለስልጣኑ በትኩረት አይቶ ሊፈታ ይገባል ብለዋል።
ባለስልጣኑ ያለበትን የወሰን ማስከበር ችግር፣ በመሰረተ ልማቱ ላይ እደረሰ ያለውን ጉዳት እና ስርቆት ከማስቀረት አኳያ ደንቦች እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል።
አዳዲስ የውሃ ጉድጓዶች ላይ ያለውን የኤሌትሪክ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በ10 ቀን ውስጥ ምላሽ እንደሚያገኝ የአዲስ አበባ ኤሌትሪክ አገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ገበየሁ ሊካሳ በዚሁ ወቅት አረጋግጠዋል።
ውይይቱን የመሩት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሞላ ንጉስ መድረኩ እንዲያው ተገናኝቶ ለመለያየት ሳይሆን በየደረጃው ያሉ የምክር ቤት አባላት ፣ ባለሞያዎች እና አመራሮች ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እና ችግር ፈቺ ለመሆን እንዲቻል በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል።
አቶ ሞላ አክለውም ተቋማቱ ያሉባቸውን ችግሮች በመፍታት በኩል በየደረጃው ያለው የምክር ቤት መዋቅር ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።