ጉብኝቱ የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ፣ የለገዳዲ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ እና የባለሥልጣኑን የስልጠና ማዕከል ያካተተ ሲሆን በጉብኝቱ ብዙ ግንዛቤ ማግኘታቸውን አስረድተዋል።

ከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የተውጣጡት ባለሙያዎች በጎበኙት የውሃም ሆነ የፍሳሽ ስራ አድካሚ ከፍተኛ  ድካም አንዳለው ተረድተናል ብለዋል።

በሁሉም ጉብኝት ጥሩ ግንዛቤ አግኝተናል ያሉት ጉብኚዎቹ ግንዛቤያቸውን ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በማካፈል የተቋሙ አምባሳደር እንደሚሆኑም አረጋግጠዋል ።

በተለይም በውሃ ቁጠባ ዙሪያ እና ባዕድ ነገሮችን የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ውስጥ ባለመጨመር ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡም ቃል ገብተዋል። .