ቋሚ ኮሚቴው የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን እያሰራው የሚገኘውን የሳውዝ አያት ኖርዝ ፈንታ የውሃ ፕሮጀክት እና የኮዬ ፈጬን ያልተማከለ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ባሳለፍነው ቅዳሜ ነው የመስክ ጉብኝት ያደረገው ፡፡

የተጎበኘው የሳውዝ አያት ኖርዝ ፈንታ የውሃ ፕሮጀክት ፊዚካል ግንባታ 70 በመቶ የደረሰ ሲሆን ሲጠናቀቅ 68 ሺህ ሜ.ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ያለው እና ከ700ሺኅ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ፡፡

በሌላ በኩል በመጠናቀቅ ላይ ያለው የኮዬ ፈጬ ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የተጎበኘ ሲሆን የፕሮጀክቱም በአካባቢው የሚገቡ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ቢሆንም፤

እስካሁን ሙሉ በሙሉ ባለመግባታቸው የፕሮጀክቱን ጥራት ሙከራ ለማድረግ በቂ ፍሳሽ ያለማግኘት ችግር እንቅፋት እንደፈጠረ የባለስልጣኑ የውሃና ሳኒቴሽን ልማትና ማስፋፊያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ስዩም ቶላ ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም መልካም ነው ያሉት የምክር ቤቱ የትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ይሳቅ ግርማይ በቀጣይ ከኮንትራት አስተዳደር ጋር ያሉ የተለያዩ ማነቆዎች በጊዜ ተፈተው የከተማው ነዋሪዎችን በወቅቱ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡