ባለስልጣኑ ዉይይቱን ፦ ዘመናዊ የፍሳሽ መስመር በተዘረጋባቸው አካባቢ ነዋሪዎች እና የስምንቱ ቅ/ጽ/ቤት የፎረም አመራሮች ጋር ነው ዛሬ በራስ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሄደው ።

የውይይቱ አላማ መስመሩ የተዘረጋባቸው አካባቢ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሶስት ሜትር ርቀት ድረስ የተዘረጋውን መስመር የቤት ለቤት ቅጥያ (መስመር በማገናኘት )ተጠቃሚ እንዲሆኑ ንቅናቄ ለመፍጠር ነው።

ከዚህም በተጨማሪ የፍሳሽ አወጋገዱን እየተፈታተኑ ያሉትን ህገ ወጥ ተግባራት ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ከባለስልጣኑ ጎን በመቆም ሀብቱን እንዲጠብቅ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ።

በዉይይቱም ዘመናዊ የፍሳሽ አወጋገድ አሁን ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ፣ እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎች ምንድናቸው የሚሉ መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።

ተሳታፊዎችም በባለስልጣኑ ከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የፍሳሽ መሰረተ ልማት ተጠቃሚ ለመሆን የግንዛቤ ስራ መስራት ፤ የማንሆል ክዳን በቶሎ መክደን መስመሩ ያልተዳረሰባቸውን አካባቢዎች ማዳረስ ከባለስልጣኑ የሚጠበቅ እንደሆነ ተነስቷል ።

ስርቆቱን መከላከል ፤ንብረቱን በባለቤትነት መጠበቅ እና በተዘረጉ መስመሮች ቅጥያ በማሰራት መጠቀም ከነዋሪው የሚጠበቅ እንደሆነ እና በትብብር መስራት እንሚያስፈልግ መግባባት ላይ ተደርሷል ።