በተለምዶ ሀያሁለት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የንግድ ስራ የሚያከናውነው አዝመራ ሽሮ ተብሎ የሚጠራው ድርጅት እና ቦሌ አትላስ አካባቢ የሚገኘው ሴንቸሪ አዲስ ሪል እስቴት የተባለው ተቋም በህገወጥ መንገድ የውሃ ቆጣሪ በማንሳት ለባለስልጣኑ ይገባ የነበረውን ገቢ በማስቀረታቸው  እርምጃ እንደተወሰዳቸው በባለስልጣኑ የመገናኛ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ አህመድ መሀመድ ገልጸዋል፡፡

ህገወጥ ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ በቀን ሊጠቀሙ የሚችሉትን አማካይ ፍጆታ እና ለምን ያህል ጊዜ ድርጊቱን እንደፈጸሙ በማስላት አዝመራ ሽሮ በ165 ሺህ 689 ብር እንዲሁም  ሴንቸሪ አዲስ ሪል እስቴት 126 ሺህ 137 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል ፡፡

ባለስልጣኑ በቀጣይ መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን ለመከለከል በቁርጠኝነት አየሰራ እንደሆነ አቶ አህመድ አመልክተዋል፡፡

ባለስልጣኑ በሌሎች አካባቢዎችም መሰል ተግባር የሚፈጽሙ አካላት ላይ እርምጃ ለመውስድ የማጣራት ስራ እየተሰራ ሲሆን፤

ደንበኞችም በህገወጥ ተግባር ውስጥ ከመሳተፍ በመቆጠብና ህገወጥ አከላት በመጠቆም ውስን የሆነውን የውሃ ሀብት ከብክነት በመከላከል የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

 

(የአዲስ አበባ ዉሃ እና ፍሳሽ ባስልጣን በኮሙኒኬሽን የስራ ሂደት)