በባለስልጣኑ በበጀት አመቱ 104 የጋራ 26 ተንቀሳቃሽ እና  15 የህዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ የባለስልጣኑ የፍሳሽ ደንበኞች ንዑስ የስራ ሂደት መሪ አቶ ኃይለእየሱስ ደናነው ገልጸዋል፡፡

መጸዳጃ ቤቶችን የሚገነባው ከክፍለ ከተሞች መሬት አሰተዳደር መሬት በማስፈቀድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ  ባቀረበው ጥያቄ መሰረት  ለጋራ መገልገያ የሚሆን 104 መሬት ለተንቀሳቃሽ 5 እንዲሁም ለህዝብ መጸዳጃ ቤት አገልግሎት 8 ቦታዎች ተለይተው መሬት ማግኘት ተችሏል፡፡

እስካሁንም ለጋራ መጸዳጃ ቤቶች በተለዩ ቦታዎች ላይ ግንባታ ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

ያም ሆኖ የዘርፉ አገልግሎት ችግሮች የተጋረጡበት ስለመሆኑ አቶ ሀይለእየሱስ ይናገራሉ ፡፡የመሬት አቅርቦት ችግር ዋንኛ የዘርፉ ማነቆ ሆኑዋል፡፡ በተገኙ መሬቶችም ላይ የወሰን ማስከበር ችግር እና ለግንባታ እና ለአገልግሎት ምቹ አለመሆን እንዲሁም ግንባታውን የሚያከናውኑ ማህበራት አቅም ውስንነት   ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው፡፡

አስካሁን በባለስልጣኑ የተገነቡ 301 መጸዳጃ ቤቶች ለመዲናዋ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን